2 ሳሙኤል 24:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 ኦርናም “ንጉሥ ሆይ! አውድማውን ወስደህ በፈቀድከው ዐይነት ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቅርብበት፤ በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት ሆነው ይቀርቡ ዘንድ እነሆ እነዚህ በሬዎች አሉ፤ ስለ ማገዶም ጉዳይ እነርሱ የሚጠመዱበት ቀንበርና የእህል መውቂያው እንጨት ሁሉ አለ” አለው። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም22 ኦርናም ዳዊትን እንዲህ አለ፤ “ንጉሥ ጌታዬ ደስ ያለውን ወስዶ መሥዋዕቱን ያቅርብ፤ ለሚቃጠል መሥዋዕት በሬዎቹን፤ ለሚነድደውም ዕንጨት፣ የመውቂያው ዕቃና የበሬ ቀንበር አለ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 ኦርናም ዳዊትን እንዲህ አለ፤ “ንጉሥ ጌታዬ ደስ ያለውን ወስዶ መሥዋዕቱን ያቅርብ፤ ለሚቃጠል መሥዋዕት በሬዎች፥ ለሚነደውም ዕንጨት፥ የመውቂያው ዕቃና የበሬ ቀንበር አለ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 ኦርናም ዳዊትን፥ “ጌታዬ ንጉሡ በፊቱ ደስ ያሰኘውን ወስዶ ያቅርብ፤ እነሆም፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት በሬዎች፥ ለሚቃጠልም እንጨት የአውድማ ዕቃና የበሬ ዕቃ አለ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 ኦርናም ዳዊትን፦ ጌታዬ ንጉሡ እንደ ወደደ ወስዶ ያቅርብ፥ እነሆ፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት በሬዎች፥ ለሚቃጠልም እንጨት የአውድማ ዕቃና የበሬ ቀንበር አለ። Ver Capítulo |