ዳዊትም ናታንን፥ “እግዚአብሔርን በድያለሁ” አለው። ናታንም ዳዊትን አለው፥ “እግዚአብሔር ደግሞ ኀጢአትህን አርቆልሃል፤ አትሞትምም።
2 ሳሙኤል 24:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቡንም ከቈጠረ በኋላ ዳዊትን ልቡ መታው፤ ዳዊትም እግዚአብሔርን፥ “ባደረግሁት ነገር እጅግ በድያለሁ፤ አሁን ግን አቤቱ! ታላቅ ስንፍና አድርጌአለሁና የባሪያህን ኀጢአት ታርቅ ዘንድ እለምንሃለሁ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት ተዋጊዎቹን ከቈጠረ በኋላ ኅሊናው ስለ ወቀሠው፣ “ባደረግሁት ነገር ታላቅ ኀጢአት ሠርቻለሁ፤ አሁንም እግዚአብሔር ሆይ፤ የአገልጋይህን በደል እንድታርቅ እለምንሃለሁ፤ የፈጸምሁት ታላቅ የስንፍና ሥራ ነውና” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊት ሕዝቡን ከቆጠረ በኋላ ኅሊናው ወቀሰው፤ ዳዊትም ጌታን፥ “ባደረግሁት ነገር የፈጸምኩት ታላቅ ኃጢአት ነው፤ አሁን ግን፥ ጌታ ሆይ፤ የአገልጋይህን በደል ይቅር እንድትል እለምንሃለሁ፤ የፈጸምኩት ታላቅ የሞኝነት ሥራ ነውና” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ዳዊት ሕዝቡን ከቈጠረ በኋላ የኅሊና ወቀሳ ስላስጨነቀው እግዚአብሔርን “እኔ ይህን በማድረጌ ታላቅ በደል ፈጽሜአለሁ፤ የሞኝነት ሥራ ስለ ሠራሁም እባክህ ይቅር በለኝ!” ሲል ለመነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቡንም ከቈጠረ በኋላ ዳዊትን ልቡ መታው፥ ዳዊትም እግዚአብሔርን፦ ባደረግሁት ነገር እጅግ በድያለሁ፥ አሁን ግን፥ አቤቱ፥ ታላቅ ስንፍና አድርጌአለሁና የባሪያህን ኃጢአት ታርቅ ዘንድ እለምንሃለሁ አለው። |
ዳዊትም ናታንን፥ “እግዚአብሔርን በድያለሁ” አለው። ናታንም ዳዊትን አለው፥ “እግዚአብሔር ደግሞ ኀጢአትህን አርቆልሃል፤ አትሞትምም።
ዳዊትም ሕዝቡን የሚመታውን መልአክ ባየ ጊዜ እግዚአብሔርን፥ “እነሆ፥ እኔ በድያለሁ፤ ክፉም ሥራ እኔ አድርጌአለሁ፤ እነዚህ በጎች ግን ምን አደረጉ? እጅህ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ ትሆን ዘንድ እለምንሃለሁ” ብሎ ተናገረው።
“አንተን ስለ በደሉ ሰማይ ቢዘጋ፥ ዝናብም ባይዘንብ፥ በዚህም ስፍራ ቢጸልዩ፥ ለስምህም ቢናዘዙ፥ ባስጨነቅሃቸውም ጊዜ ከኀጢአታቸው ቢመለሱ፥
ዳዊትም እግዚአብሔርን፥ “ይህን በማድረግ እጅግ በድያለሁ፤ አሁንም ታላቅ ስንፍና አድርጌአለሁና የባሪያህን ኀጢአት ታስወግድ ዘንድ እለምንሃለሁ” አለው።
እግዚአብሔር ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ያጸና ዘንድ ዐይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። አሁንም ባለማወቅህ በድለሃል፤ ስለዚህም ከዛሬ ጀምሮ ጦርነት ይሆንብሃል።”
ሕዝቅያስም በኢየሩሳሌም ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ስለ ልቡ ኵራት ሰውነቱን አዋረደ፤ እግዚአብሔርም በሕዝቅያስ ዘመን ቍጣውን አላመጣባቸውም።
ስለ ምን መተላለፌን ይቅር አትልም? ኀጢአቴንስ ስለ ምን አታነጻም? አሁን በምድር ውስጥ እተኛለሁ፤ በማለዳም አልነቃም።”
በማግሥቱም ዮሐንስ ወደ እርሱ ሲመጣ ጌታችን ኢየሱስን አይቶ እንዲህ አለ፤ “እነሆ፥ የዓለሙን ኀጢኣት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።
እነርሱ ግን ይህን በሰሙ ጊዜ ኅሊናቸው ወቅሶአቸው ከሽማግሌዎች ጀምሮ እስከ ኋለኞቹ ድረስ፥ አንዳንድ እያሉ ወጡ፤ ጌታችን ኢየሱስም ብቻውን ቀረ፤ ሴትዮዪቱም በመካከል ቆማ ነበር።
ደንቆሮ፥ ብልሃተኛም ያልሆንህ ሕዝብ ሆይ፥ ለእግዚአብሔር ይህን ትመልሳለህን? የፈጠረህ አባትህ አይደለምን? የፈጠረህና ያጸናህ እርሱ ነው።
እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት የምንኖር፥ የምንጣላ፥ እርስ በርሳችን የምንጠላላ ነበርን።
ሳሙኤልም ሳኦልን፥ “በድለኻል፤ አምላክህ እግዚአብሔር ያዘዘህን ትእዛዙን አልጠበቅህምና፤ ዛሬ እግዚአብሔር መንግሥትህን በእስራኤል ላይ ለዘለዓለም አጽንቶልህ ነበር።
የዳዊትም ሰዎች፥ “እነሆ፥ ጠላትህን በእጅህ አሳልፌ እሰጠዋለሁ፤ በዐይንህም ደስ የሚያሰኝህን ታደርግበታለህ ብሎ እግዚአብሔር የነገረህ ቀን እነሆ ዛሬ ነው” አሉት። ዳዊትም ተነሥቶ የሳኦልን መጐናጸፊያ ዘርፍ በቀስታ ቈረጠ።
ሳኦልም፥ “በድያለሁ፤ ልጄ ዳዊት ሆይ! ተመለስ፤ ዛሬ ነፍሴ በዐይንህ ፊት ከብራለችና ከዚህ በኋላ ክፉ አላደርግብህም፤ እነሆ፥ ስንፍና እንደ አደረግሁና፥ እጅግ ብዙም እንደ ሳትሁ ዐወቅሁ” አለ።