2 ሳሙኤል 22:51 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የንጉሡን መድኀኒት ታላቅ ያደርጋል፤ ቸርነቱንም ለቀባው ለዳዊትና ለዘሩ፥ ለዘለዓለም ያደርጋል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለንጉሡ ታላቅ ድል ይሰጠዋል፤ ለቀባው ለዳዊትና ለዘሩ፣ ለዘላለም የማይለወጥ ፍቅሩን ያሳየዋል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለንጉሡ ታላቅ ድል ይሰጠዋል፤ ለቀባው ለዳዊትና ለዘሩ፥ የማይለወጥ ፍቅሩን ያሳያል፥ ይህንንም ለዘለዓለም ያደርጋል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ላነገሠው ንጉሥ ድልን ያጐናጽፈዋል፤ እርሱ ከቀባውም ዘለዓለማዊ ፍቅሩን ያሳየዋል፤ ለዳዊትና ለዘሩ፥ ለዘለዓለም ይህን ያደርጋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የንጉሡን መድኃኒት ታላቅ ያደርጋል፥ ቸርነቱንም ለቀባው፥ ለዳዊትና ለዘሩ፥ ለዘላለም ይሰጣል። |
የዳዊትም የመጨረሻ ቃሉ ይህ ነው። እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ያደረገው፥ የያዕቆብም አምላክ የቀባው፥ የታማኙ ሰው፥ በእስራኤል ዘንድ መልካም ባለመዝሙር የሆነው፥ የታማኙ የእሴይ ልጅ የዳዊት ንግግር ይህ ነው፤