2 ሳሙኤል 21:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስራኤልንም በተገዳደረ ጊዜ የዳዊት ወንድም የሴማይ ልጅ ዮናታን ገደለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም እስራኤልን በተገዳደረ ጊዜ፣ የዳዊት ወንድም የሳምዓ ልጅ ዮናታን ገደለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም ሰው እስራኤልን በተገዳደረ ጊዜ፥ የዳዊት ወንድም የሻማ ልጅ ዮናታን ገደለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም እስራኤላውያንን በብርቱ ተፈታተነ፤ ይሁን እንጂ እርሱን የዳዊት ወንድም የሻማ ልጅ ዮናታን ገደለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስራኤልንም በተገዳደረ ጊዜ የዳዊት ወንድም የሣማ ልጅ ዮናታን ገደለው። |
ደግሞም በጌት ላይ ጦርነት ሆነ፤ በዚያም በእጁና በእግሩ ስድስት ስድስትሁላሁሉ ሃያ አራት ጣቶች የነበሩት አንድ ረዥም ሰው ነበረ፤ እርሱ ደግሞ ከራፋይም የተወለደ ነበረ።
እነዚያም አራቱ በጌት ውስጥ ከረዐይት የተወለዱ የራፋይም ወገኖች ነበሩ፤ በዳዊትም እጅ በአገልጋዮቹም እጅ ወደቁ።
አስተዋይና ጸሓፊ የነበረው በአባቱ በኩል የዳዊት አጎት ዮናታን አማካሪ ነበረ፤ የአክማኔም ልጅ ኢያሔኤል ከንጉሡ ልጆች ጋር ነበረ፤
ፍልስጥኤማዊውም፥ “ዛሬ የእስራኤልን ጭፍሮች ተገዳደርኋቸው፤ አንድ ሰው ስጡኝ ሁለታችንም ለብቻችን እንዋጋ አልኋቸው” አለ።
ፍልስጥኤማውያንም በአንድ ወገን በተራራ ላይ ቆመው ነበር፥ እስራኤልም በሌላው ወገን በተራራ ላይ ቆመው ነበር፤ በመካከላቸውም ሸለቆ ነበረ።
እኔ ባሪያህ አንበሳና ድብ ገደልሁ፤ ይህም ያልተገረዘው ፍልስጥኤማዊ ከእነርሱ እንደ አንዱ ይሆናል። እንግዲህ እገድለው ዘንድ፥ ከእስራኤልም ተግዳሮትን አስወግድ ዘንድ ዛሬ አልሄድምን? የሕያው አምላክ ጭፍሮችን ይገዳደር ዘንድ ይህ ቈላፍ ምንድን ነው?”