እነሆም፥ ዘመዶች ሁሉ በባሪያህ ላይ ተነሡ፤ ስለ ገደለው ስለ ወንድሙ ነፍስ እንገድለው ዘንድ ወንድሙን የገደለውን አውጪ አሉኝ፤ እንዲሁም ደግሞ ለባሌ ስምና ዘር በምድር ላይ እንዳይቀር ወራሹን የቀረውን መብራቴን ያጠፋሉ፤”
2 ሳሙኤል 21:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሶርህያም ልጅ አቢሳ አዳነው፤ ፍልስጥኤማዊውንም ወግቶ ገደለው። ያንጊዜም የዳዊት ሰዎች፥ “አንተ የእስራኤል መብራት እንዳትጠፋ ከእንግዲህ ወዲህ ከእኛ ጋር ለሰልፍ አትወጣም” ብለው ማሉለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጽሩያ ልጅ አቢሳ ግን ዳዊትን ለመታደግ መጣ፤ ፍልስጥኤማዊውንም ወግቶ ገደለው። ከዚያም የዳዊት ሰዎች፣ “የእስራኤል መብራት እንዳይጠፋ ከእንግዲህ አንተ ከእኛ ጋራ ወደ ጦርነት መውጣት የለብህም” ብለው ማሉለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጽሩያ ልጅ አቢሳ ግን ዳዊትን ለመታደግ መጣ፤ ፍልስጥኤማዊውንም መትቶ ገደለው። ከዚያም የዳዊት ሰዎች፥ “የእስራኤል መብራት እንዳይጠፋ ከእንግዲህ አንተ ከእኛ ጋር ወደ ጦርነት መውጣት የለብህም” ብለው ማሉለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን የጸሩያ ልጅ አቢሳ ዳዊትን ለመርዳት መጥቶ በዚያ ኀያል ሰው ላይ አደጋ በመጣል ገደለው፤ ከዚያን በኋላ የዳዊት ተከታዮች ዳግመኛ ከእነርሱ ጋር ወደ ጦርነት እንዳይሄድ ዳዊትን ቃል በማስገባት “የእስራኤል መብራት የሆንክ አንተ እንዳትጠፋ ዳግመኛ ወደ ጦርነት አትወጣም” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጽሩያም ልጅ አቢሳ አዳነው፥ ፍልስጥኤማዊውንም መትቶ ገደለው። ያንጊዜም የዳዊት ሰዎች፦ አንተ የእስራኤልን መብራት እንዳታጠፋ ከእንግዲህ ወዲህ ከእኛ ጋር ለሰልፍ አትወጣም ብለው ማሉለት። |
እነሆም፥ ዘመዶች ሁሉ በባሪያህ ላይ ተነሡ፤ ስለ ገደለው ስለ ወንድሙ ነፍስ እንገድለው ዘንድ ወንድሙን የገደለውን አውጪ አሉኝ፤ እንዲሁም ደግሞ ለባሌ ስምና ዘር በምድር ላይ እንዳይቀር ወራሹን የቀረውን መብራቴን ያጠፋሉ፤”
ዳዊትም ሕዝቡን ከኢዮአብ እጅ በታች ሢሶውን፥ ከኢዮአብም ወንድም ከሶርህያ ልጅ ከአቢሳ እጅ በታች ሢሶውን፥ ከጌት ሰውም ከኤቲ እጅ በታች ሢሶውን ላከ። ዳዊትም ሕዝቡን፥ “እኔ ደግሞ ከእናንተ ጋር እወጣለሁ” አላቸው።
እነርሱ ግን “አንተ ከእኛ ከሁላችን ይልቅ እንደ ዐሥር ሽህ ሠራዊት ስለሆንህ ብንሸሽ ልባቸው አይከተለንምና፥ እኩሌታችንም ብንሞት ልባቸው አይከተለንምና አትውጣ፤ አሁንም መርዳትን ትረዳን ዘንድ በከተማ ብትኖርልን ይሻለናል” አሉት።
ስሜንም ባኖርሁባት በዚያች በመረጥኋት ከተማ በኢየሩሳሌም ለባሪያዬ ለዳዊት በፊቴ ሁልጊዜ መብራት ይሆንለት ዘንድ ለልጁ ሁለት ነገድን እሰጠዋለሁ።
ነገር ግን ልጁን ከእርሱ በኋላ ያስነሣ ዘንድ፥ ኢየሩሳሌምንም ያጸና ዘንድ አምላኩ እግዚአብሔር ስለ ዳዊት በኢየሩሳሌም መብራትን አደረገለት፤
የቃርሔም ልጅ ዮሐናን፥ “እባክህ፥ ልሂድ፤ ማንም ሳያውቅ የናታንያን ልጅ እስማኤልን ልግደለው፤ ወደ አንተ የተሰበሰቡ አይሁድ ሁሉ እንዲበተኑ፥ የይሁዳም ቅሬታ እንዲጠፋ ነፍስህን ስለ ምን ይገድላል?” ብሎ በመሴፋ በቈይታ ለጎዶልያስ ተናገረ።