ለአሚሳይም፦ አንተ የአጥንቴ ፍላጭና የሥጋዬ ቍራጭ አይደለህምን? በዘመንህም ሁሉ በኢዮአብ ፋንታ በፊቴ የሠራዊት አለቃ ሳትሆን ብትቀር ዛሬ እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ፤ ይህንም ይጨምርብኝ በሉት።”
2 ሳሙኤል 20:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሜሳይም የይሁዳን ሰዎች ሁሉ ይጠራ ዘንድ ሄደ፤ ነገር ግን ዳዊት የቀጠረውን ቀን አሳልፎ ዘገየ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሜሳይ ይሁዳን ለመጥራት ሄደ፤ ነገር ግን ንጉሡ ከወሰነው ጊዜ በላይ ቈየ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አማሳይ ይሁዳን ለመጥራት ሄደ፤ ነገር ግን ንጉሡ ከወሰነው ጊዜ በላይ ቆየ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐማሣም ሊጠራቸው ሄደ፤ ነገር ግን ንጉሡ በቀጠረው ቀን ተመልሶ ሊመጣ አልቻለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሜሳይም የይሁዳን ሰዎች ሁሉ ይጠራ ዘንድ ሄደ፥ ነገር ግን እርሱ የተቀጠረውን ቀን አሳልፎ ዘገየ። |
ለአሚሳይም፦ አንተ የአጥንቴ ፍላጭና የሥጋዬ ቍራጭ አይደለህምን? በዘመንህም ሁሉ በኢዮአብ ፋንታ በፊቴ የሠራዊት አለቃ ሳትሆን ብትቀር ዛሬ እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ፤ ይህንም ይጨምርብኝ በሉት።”
ዳዊትም አቢሳን፥ “አሁን አቤሴሎም ከአደረገብን ይልቅ የከፋ የሚያደርግብን የቢኮሪ ልጅ ሳቡሄ ነው፤ እርሱ የተመሸጉትን ከተሞች አግኝቶ ከዐይናችን እንዳይሰወር፥ አንተ የጌታህን ብላቴኖች ወስደህ አሳድደው” አለው።
ሳኦልም ሳሙኤል እንደ ቀጠረው ጊዜ ሰባት ቀን ቈየ፤ ሳሙኤል ግን ወደ ጌልጌላ አልመጣም፤ ሕዝቡም ከእርሱ ተለይተው ተበታተኑ።
እንዲህም ሆነ በነጋው ዮናታን ከዳዊት ጋር ምልክት ለማድረግ ወደ ተቃጠረበት ቦታ ወደ ሜዳ ወጣ፤ ከእርሱም ጋር ታናሽ ብላቴና ነበረ።