La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 19:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አንተ የሚ​ጠ​ሉ​ህን ትወ​ድ​ዳ​ለህ፤ የሚ​ወ​ድ​ዱ​ህ​ንም ትጠ​ላ​ለህ፤ አለ​ቆ​ች​ህና አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ እን​ደ​ማ​ይ​ጠ​ቅ​ሙህ እን​ደ​ም​ታ​ስብ ዛሬ ገል​ጠ​ሃ​ልና፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም ድኖ ቢሆን ዛሬ እኛ ሁላ​ችን እን​ሞት እንደ ነበር አው​ቃ​ለሁ። ይህ በፊ​ትህ ላንተ ቀና ነበ​ረና።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የሚጠሉህን ትወድዳለህ፤ የሚወድዱህን ትጠላለህ፤ የጦር አዛዦችህና ወታደሮቻቸው ለአንተ ምንህም እንዳይደሉ ይኸው ዛሬ ግልጽ አድርገሃል፤ ዛሬ አቤሴሎም በሕይወት ኖሮ እኛ ሁላችን ዐልቀን ቢሆን ደስ እንደሚልህ በዛሬው ዕለት ለማየት በቅቻለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዚያም ኢዮአብ ወደ ንጉሡ ቤት ገብቶ እንዲህ አለው፤ “የአንተን፥ የወንዶችንና የሴቶች ልጆችህን፥ የሚስቶችህንና የዕቁባቶችህን ሕይወት ያተረፉትን ሰዎች ሁሉ ዛሬ አሳፍረሃቸዋል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አንተ የሚወዱህን ትጠላለህ፤ የሚጠሉህን ግን ትወዳለህ! ስለ ጦር መኰንኖችህና ስለ ወታደሮችህ ሁሉ ምንም የማይገድህ መሆኑን በግልጥ አሳይተሃል፤ አቤሴሎም በሕይወት ቢኖርና እኛ ሁላችን ብንጠፋ ኖሮ እጅግ እንደምትደሰት ተገንዝቤአለሁ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አንተ የሚጠሉህን ትወድዳለህ፦ የሚወድዱህንም ትጠላለህ። መሳፍንትህና ባሪያዎችህን እንዳታስብ ዛሬ ገልጠሃል፥ ዛሬ ሁላችን ሞተን ቢሆን ኖር አቤሴሎምም ድኖ ቢሆን ኖሮ ደስ ያሰኘህ እንደ ነበረ ዛሬ አያለሁ።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 19:6
6 Referencias Cruzadas  

ኢዮ​አ​ብም ወደ ንጉሡ ወደ ቤት ገብቶ እን​ዲህ አለ፥ “ዛሬ ነፍ​ስ​ህ​ንና የወ​ን​ዶ​ች​ንና የሴ​ቶች ልጆ​ች​ህን ነፍስ፥ የሚ​ስ​ቶ​ች​ህ​ንና የቁ​ባ​ቶ​ች​ህን ነፍስ ያዳ​ኑ​ትን የአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህን ሁሉ ፊት በዚች ቀን አሳ​ፍ​ረ​ሃል።


አሁ​ንም ተነ​ሥ​ተህ ወጥ​ተህ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ በል​ባ​ቸው የሚ​ገባ ነገር ንገ​ራ​ቸው። ዛሬ ወደ እነ​ርሱ ካል​ወ​ጣህ በዚች ሌሊት አንድ ሰው ስንኳ ከአ​ንተ ጋር የሚ​ያ​ድር እን​ዳ​ይ​ኖር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እም​ላ​ለሁ፤ ከሕ​ፃ​ን​ነ​ትህ ጀምሮ እስ​ከ​ዚች ቀን ድረስ ካገ​ኘህ መከራ ሁሉ ዛሬ የም​ታ​ገ​ኝህ መከራ እን​ድ​ት​ከ​ፋ​ብህ እን​ግ​ዲህ አንተ ለራ​ስህ ዕወቅ” አለው።


ንጉ​ሡን፦ በደ​ለኛ ነህ የሚ​ለው፥ መኳ​ን​ን​ቱ​ንም፦ ክፉ​ዎች ናችሁ የሚ​ላ​ቸው ኀጢ​አ​ተኛ ነው


ጳው​ሎ​ስም፥ “ወን​ድ​ሞች፥ ሊቀ ካህ​ናት መሆ​ኑን አላ​ው​ቅም መጽ​ሐፍ ‘በሕ​ዝ​ብህ አለቃ ላይ ክፉ አት​ና​ገር’ ይላ​ልና” አላ​ቸው።