La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 19:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የሶ​ር​ህያ ልጅ አቢሳ ግን፥ “ሳሚ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቀ​ባ​ውን ሰድ​ቦ​አ​ልና እን​ግ​ዲህ ሞት የተ​ገ​ባው አይ​ደ​ለ​ምን?” ብሎ መለሰ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም የጽሩያ ልጅ አቢሳ፣ “ሳሚ በእግዚአብሔር የተቀባውን የረገመ ስለ ሆነ፣ መሞት አይገባውምን?” አለ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እኔ አገልጋይህ ኃጢአት መሥራቴን አውቃለሁና፤ እነሆ፥ ዛሬ ግን ጌታዬ ንጉሡን ለመቀበል ከዮሴፍ ቤት ሁሉ የመጀመሪያ ሆኜ መጥቻለሁ።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የጸሩያ ልጅ አቢሳም “እግዚአብሔር ቀብቶ ያነገሠውን ስለተሳደበ ሺምዒ በሞት መቀጣት ይገባዋል” ሲል ተናገረ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የጽሩያ ልጅ አቢሳ ግን፦ ሳሚ እግዚአብሔር የቀባውን ሰድቦአልና ሞት የተገባው አይደለምን? አለ።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 19:21
10 Referencias Cruzadas  

ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም በመ​ን​ገድ ይሄዱ ነበር፤ ሳሚም በተ​ራ​ራው አጠ​ገብ በአ​ቅ​ራ​ቢ​ያው ይሄድ ነበር፤ ሲሄ​ድም ይረ​ግ​መው፥ ድን​ጋ​ይም ይወ​ረ​ው​ር​በት ነበር፤ ትቢ​ያም ይበ​ት​ን​በት ነበር።


ንጉሡ ዳዊ​ትም ወደ በው​ሪም መጣ፤ እነ​ሆም፥ ሳሚ የሚ​ባል የጌራ ልጅ ከሳ​ኦል ቤተ ዘመድ የሆነ አንድ ሰው ከዚያ ወጣ፤ እየ​ሄ​ደም ይረ​ግ​መው ነበር።


የሶ​ር​ህያ ልጅ አቢ​ሳም ንጉ​ሡን አለው፥ “ይህ የሞተ ውሻ ጌታ​ዬን ንጉ​ሡን ስለ​ምን ይረ​ግ​ማል? ልሻ​ገ​ርና ራሱን ልቍ​ረ​ጠው፤”


ነገር ግን ክብር በም​ድ​ራ​ችን ያድር ዘንድ ማዳኑ ለሚ​ፈ​ሩት ቅርብ ነው።


“ፈራ​ጆ​ችን አት​ስ​ደብ፥ የሕ​ዝ​ብ​ህ​ንም አለቃ ክፉ አት​ና​ገ​ረው።


ሬስ። ስለ እርሱ፥ “በአ​ሕ​ዛብ ውስጥ በጥ​ላው በሕ​ይ​ወት እን​ኖ​ራ​ለን” ያል​ነው፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀባ፥ የሕ​ይ​ወ​ታ​ችን እስ​ት​ን​ፋስ፥ በወ​ጥ​መ​ዳ​ቸው ተያዘ።


ከዚ​ያም በኋላ እን​ዲህ ሆነ፤ የሳ​ኦ​ልን የል​ብ​ሱን ዘርፍ ስለ ቈረጠ የዳ​ዊት ልብ በኀ​ዘን ተመታ።


ዳዊ​ትም አቢ​ሳን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀ​ባው ላይ እጁን የሚ​ዘ​ረጋ ንጹሕ አይ​ሆ​ን​ምና አት​ግ​ደ​ለው” አለው።