ንጉሡም ደግሞ ካህኑን ሳዶቅን፥ “እነሆ፥ አንተና ልጅህ አኪማኦስ፥ የአብያታርም ልጅ ዮናታን፥ ሁለቱ ልጆቻችሁ ከእናንተ ጋር በሰላም ወደ ከተማ ተመለሱ።
2 ሳሙኤል 18:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሳዶቅ ልጅ አኪማሖስ ግን፥ “እግዚአብሔር ከጠላቶቹ እጅ እንደ ፈረደለት ፈጥኜ ሄጄ ለንጉሥ የምሥራች ልንገርን?” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ የሳዶቅ ልጅ አኪማአስ፣ “እግዚአብሔር ጠላቶቹን የተበቀለለት መሆኑን ሮጬ ሄጄ ለንጉሡ የምሥራች ልንገረው” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ የሳዶቅ ልጅ አሒማዓጽ፥ “ጌታ ጠላቶቹን የተበቀለለት መሆኑን ሮጬ ሄጄ ለንጉሡ የምሥራች ልንገረው” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ የሳዶቅ ልጅ አሒማዓጽ ኢዮአብን “እግዚአብሔር ከጠላቶቹ እንዳዳነው የሚገልጠውን መልካም ወሬ ይዤ ወደ ንጉሡ ልሩጥ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሳዶቅ ልጅ አኪማአስ ግን፦ እግዚአብሔር ጠላቶቹን እንደተበቀለለት ሮጬ ለንጉሥ የምሥራች ልንገር አለ። |
ንጉሡም ደግሞ ካህኑን ሳዶቅን፥ “እነሆ፥ አንተና ልጅህ አኪማኦስ፥ የአብያታርም ልጅ ዮናታን፥ ሁለቱ ልጆቻችሁ ከእናንተ ጋር በሰላም ወደ ከተማ ተመለሱ።
እነሆ፥ የሳዶቅ ልጅ አኪማኦስና የአብያታር ልጅ ዮናታን፥ ልጆቻቸው በዚያ ከእነርሱ ጋር አሉ፤ የምትሰሙትን ሁሉ በእነርሱ እጅ ላኩልኝ።”
ዮናታንና አኪማሆስም በሮጌል ምንጭ አጠገብ ቆመው ሳለ አንዲት ብላቴና ሄዳ ነገረቻቸው፤ ወደ ከተማ መግባት አልተቻላቸውም ነበርና፤ እነርሱም ሄደው ለንጉሡ ለዳዊት ነገሩት።
ኢዮአብም፥ “አንተ በዚች ቀን የምሥራች የምትናገር ሰው አይደለህም፤ ወሬውን በሌላ ቀን ትናገራለህ፤ በዚች ቀን ግን የንጉሡ ልጅ እንደ ሞተ ወሬ አትናገርም” አለው።
እርሱም፥ “እኔ ብሮጥ ምን ይገድዳል?” አለ። እርሱም፥ “ሩጥ” አለው። አኪማሖስም በሰርጥ ጎዳና በኩል ሮጠ፤ ኩሲንም ቀደመው።
እነሆም፥ ኩሲ መጣ፤ ኩሲም፥ “እግዚአብሔር በላይህ የተነሡትን ሁሉ ዛሬ እንደ ተበቀለልህ ለጌታዬ ለንጉሡ ወሬ አምጥቻለሁ” አለ።
ለባቢሎን ንጉሥ ይነግር ዘንድ ሯጩ ሯጩን ለመገናኘት፤ መልእክተኛውም መልእክተኛውን ለመገናኘት ይሮጣል፤ ከተማዋ ከዳር እስከ ዳር ተይዛለችና፤
ወንድሞቻችን፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፤ ቍጣን አሳልፏት፥ “እኔ እበቀላለሁ፤ እኔ ብድራትን እከፍላለሁ ይላል እግዚአብሔር” ተብሎ ተጽፎአልና።