2 ሳሙኤል 18:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)31 እነሆም፥ ኩሲ መጣ፤ ኩሲም፥ “እግዚአብሔር በላይህ የተነሡትን ሁሉ ዛሬ እንደ ተበቀለልህ ለጌታዬ ለንጉሡ ወሬ አምጥቻለሁ” አለ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም31 ከዚያም ኢትዮጵያዊው ደርሶ፣ “ንጉሥ ጌታዬ ሆይ፤ የምሥራች! ዛሬ እግዚአብሔር ከተነሡብህ ጠላቶችህ ሁሉ ታድጎሃል” አለው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)31 ከዚያም ኢትዮጵያዊው ደርሶ፥ “ንጉሥ ጌታዬ ሆይ፤ የምሥራች! ዛሬ ጌታ ከተነሡብህ ጠላቶችህ ሁሉ ታድጎሃል” አለው። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም31 ቀጥሎም ኢትዮጵያዊው አገልጋይ እዚያ ደረሰና ንጉሡን “ንጉሥ ሆይ! የምሥራች ቃል ይዤልህ መጥቼአለሁ፤ በአንተ ላይ በዐመፅ የተነሣሡብህን ድል እንድታደርግ ዛሬ እግዚአብሔር ረድቶሃል!” አለው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)31 እነሆም፥ ኵሲ መጣ፥ ኵሲም፦ እግዚአብሔር በላይህ የተነሡትን ሁሉ ዛሬ እንደ ተበቀለልህ ለጌታዬ ለንጉሡ ወሬ አምጥቼአለሁ አለ። Ver Capítulo |