2 ሳሙኤል 17:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤሴሎምም በሠራዊቱ ላይ በኢዮአብ ስፍራ አሜሳይን ሾመ፤ አሜሳይም የኢዮአብን እናት የሶርህያን እኅት የነዓሶንን ልጅ አቢግያን የአገባው የኢይዝራኤላዊው የዮቶር ልጅ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አቤሴሎምም በኢዮአብ ምትክ አሜሳይን በሰራዊቱ ላይ ሾመ፤ አሜሳይ የእስማኤላዊው የዮቴር ልጅ ነበረ፤ ዮቴርም የኢዮአብን እናት፣ የጽሩያን እኅት፣ የናዖስን ልጅ አቢግያን አግብቶ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤሴሎምም በኢዮአብ ምትክ አማሳይን በሠራዊቱ ላይ ሾመ፤ አማሳይ የእስማኤላዊው የዮቴር ልጅ ነበረ፤ ዮቴርም የኢዮአብን እናት፥ የጽሩያን እኅት፥ የናዖስን ልጅ አቢግያንሰ አግብቶ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አቤሴሎም በኢዮአብ ምትክ ዐማሣ ተብሎ የሚጠራውን ሰው የጦር አዛዥ አድርጎ ሾመ፤ ዐማሣ የእስራኤላዊው የዬቴር ልጅ ነበር፤ እናቱም አቢጌል ተብላ የምትጠራ የናሐሽ ልጅ ስትሆን ለኢዮአብ እናት ለጸሩያ እኅት ነበረች። ዜና መ. 2፥17 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤሴሎምም በጭፍራው ላይ በኢዮአብ ስፍራ አሜሳይን ሾመ፥ አሜሳይም የይስማኤላዊ ሰው የዬቴር ልጅ ነበረ፥ እርሱም የኢዮአብን እናት የጽሩያን እኅት የናዖስን ልጅ አቢግያን አግብቶ ነበር። |
ለአሚሳይም፦ አንተ የአጥንቴ ፍላጭና የሥጋዬ ቍራጭ አይደለህምን? በዘመንህም ሁሉ በኢዮአብ ፋንታ በፊቴ የሠራዊት አለቃ ሳትሆን ብትቀር ዛሬ እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ፤ ይህንም ይጨምርብኝ በሉት።”
የይሁዳንም ሰዎች ሁሉ ልብ እንደ አንድ ሰው ልብ አድርጎ አዘነበለ፤ ወደ ንጉሡም፥ “አንተና ብላቴኖችህ፥ አገልጋዮችህም ሁሉ ተመለሱ” ብለው ላኩበት።
ለሶርህያ ልጅ ለኢዮአብም ወሬ ደረሰለት፤ ኢዮአብ ከአዶንያስ ጋር ተባብሮ ተከተለው እንጂ ከሰሎሞን ጋር አልተባበረም፤ አልተከተለውምም ነበርና። ኢዮአብም ወደ እግዚአብሔር ድንኳን ሸሽቶ የመሠዊያውን ቀንድ ያዘ።
አባቴ ዳዊት ሳያውቅ ከእርሱ የሚሻሉትን ሁለቱን ጻድቃን ሰዎች፥ የእስራኤልን ሠራዊት አለቃ የኔርን ልጅ አበኔርን፥ የይሁዳንም ሠራዊት አለቃ የኢያቴርን ልጅ አሜሳይን በሰይፍ ገድሎአልና እግዚአብሔር የዐመፅ ደሙን በራሱ ላይ መለሰ።
አንተም ደግሞ የሶርህያ ልጅ ኢዮአብ፥ ሁለቱን የእስራኤል ሠራዊት አለቆች የኔር ልጅ አበኔርን የኢያቴርንም ልጅ አሜሳይን ገድሎ፥ በእኔ ላይ ያደረገውን ታውቃለህ፤ የጦርነትንም ደም በሰላም አፈሰሰ፤ በወገቡም ባለው ድግና በእግሩም ባለው ጫማ ንጹሕ ደም አኖረ።
ዳዊትም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሳኦልን ሊወጋ በመጣ ጊዜ ከምናሴ ወገን ሰዎች ወደ ዳዊት ከዱ፤ የፍልስጥኤማውያን አለቆች ግን፥ “በራሳችን ላይ ጉዳት አድርጎ ወደ ጌታው ወደ ሳኦል ይመለሳል” ሲሉ ተማክረው ሰድደውታልና እርሱ አልረዳቸውም።