ከሄዱም በኋላ እነርሱ ከጕድጓዱ ወጥተው ሄዱ፤ ለንጉሡም ለዳዊት ነገሩት፤ ዳዊትንም፥ “አኪጦፌል በእናንተ ላይ እንዲህ መክሮአልና ተነሡ፤ ፈጥናችሁም ውኃውን ተሻገሩ” አሉት።
2 ሳሙኤል 17:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትና ከእርሱም ጋር የነበሩት ሁሉ ተነሥተው ዮርዳኖስን ተሻገሩ፤ እስኪነጋም ድረስ ዮርዳኖስን ሳይሻገር አንድ ሰው እንኳን አልቀረም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ዳዊትና ዐብሮት ያለው ሕዝብ በሙሉ ተነሥቶ ዮርዳኖስን ተሻገረ፤ ሲነጋም ዮርዳኖስን ሳይሻገር የቀረ አንድም ሰው አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ዳዊትና አብሮት ያለው ሕዝብ በሙሉ ተነሥቶ ዮርዳኖስን ተሻገረ፤ ሲነጋም ዮርዳኖስን ሳይሻገር የቀረ አንድም ሰው አልነበረም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ዳዊትና ተከታዮቹ የዮርዳኖስን ወንዝ መሻገር ጀመሩ፤ እስኪነጋም ድረስ ሁሉም ወንዙን ተሻግረው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትና ከእርሱም ጋር የነበሩት ሁሉ ተነሥተው ዮርዳኖስን ተሻገሩ፥ እስኪነጋም ድረስ ዮርዳኖስን ሳይሻገር አንድ ሰው እንኳ አልቀረም። |
ከሄዱም በኋላ እነርሱ ከጕድጓዱ ወጥተው ሄዱ፤ ለንጉሡም ለዳዊት ነገሩት፤ ዳዊትንም፥ “አኪጦፌል በእናንተ ላይ እንዲህ መክሮአልና ተነሡ፤ ፈጥናችሁም ውኃውን ተሻገሩ” አሉት።
አኪጦፌልም ምክሩ እንዳልሠራ ባየ ጊዜ አህያውን ጫነ፤ ተነሥቶም ወደ ቤቱ ወደ ከተማው ሄደ፤ ቤቱንም አደራጅቶ በገዛ እጁ ታንቆ ሞተ፤ በአባቱም መቃብር ተቀበረ።