2 ሳሙኤል 17:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴቲቱም ዳውጃ ወስዳ በጕድጓዱ አፍ ላይ ዘረጋችበት፤ የተፈተገ እህልም በላዩ አሰጣችበት፤ ያወቃቸውም የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሚስቱም በጕድጓዱ አፍ ላይ የስጥ ማስጫ ዘርግታ እህል አሰጣች፤ ማንም ይህን አላወቀም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሚስቱም በጉድጓዱ አፍ ላይ የስጥ ማስጫ ዘርግታ እህል አሰጣች፤ ማንም ይህን አላወቀም ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዚያም ሰው ሚስት ጒድጓዱን ሸፍና በላዩ ላይ ማንም ሰው እንዳይጠረጥር እህል አሰጣችበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴቲቱም በጉድጓዱ አፍ ላይ ዳውጃ ዘረጋችበት፥ የተከካ እህልም በላዩ አሰጣችበት፥ ነገሩም እንዲህ ተሰወረ። |
ሙሴም ከፈርዖን ዘንድ ከከተማ ወጣ፤ እጁንም ወደ እግዚአብሔር ዘረጋ፤ ነጐድጓዱም፥ በረዶውም ጸጥ አለ፤ ዝናቡም በምድር ላይ አላካፋም።