2 ሳሙኤል 16:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡ ዳዊትም ወደ በውሪም መጣ፤ እነሆም፥ ሳሚ የሚባል የጌራ ልጅ ከሳኦል ቤተ ዘመድ የሆነ አንድ ሰው ከዚያ ወጣ፤ እየሄደም ይረግመው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሥ ዳዊት ወደ ባሑሪም ሲደርስ፣ ከሳኦል ቤተ ሰብ ነገድ የሆነ አንድ ሰው ብቅ አለ፤ እርሱም የጌራ ልጅ ሳሚ ነው፤ እየተራገመም ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሥ ዳዊት ወደ ባሑሪም ሲደርስ፥ ከሳኦል ቤተ ዘመድ የሆነ አንድ ሰው ወጣ፤ ስሙ ሺምዒ ሲሆን የጌራ ልጅ ነው፤ እየተራገመም ወደ እርሱ ይመጣ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ዳዊት ወደ ባሑሪም በደረሰ ጊዜ ከሳኦል ዘመዶች አንዱ የሆነው የጌራ ልጅ ሺምዒ ሊገናኘው ወጥቶ እየተራገመ ወደ እርሱ ቀረበ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡ ዳዊትም ወደ ብራቂም መጣ፥ እነሆም፥ ሳሚ የሚባል የጌራ ልጅ ከሳኦል ቤተ ዘመድ የሆነ አንድ ሰው ከዚያ ወጣ፥ እየሄደም ይረግመው ነበር። |
ንጉሡም ሲባን፥ “እነሆ፥ ለሜምፌቡስቴ የነበረው ሁሉ ለአንተ ይሁን” አለው። ሲባም ሰግዶ፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ በፊትህ ሞገስን ላግኝ” አለ።
ወደ ዳዊትና ወደ ንጉሡ ወደ ዳዊት አገልጋዮችም ድንጋይ ይወረውር ነበር፤ በንጉሡም ቀኝና ግራ ሕዝቡ ሁሉና ኀያላኑ ሁሉ ነበሩ።
አንድ ብላቴናም አይቶ ለአቤሴሎም ነገረው፤ እነርሱ ግን ፈጥነው ሄዱ፤ ወደ ባውሪምም ወደ አንድ ሰው ቤት መጡ፤ በግቢውም ውስጥ ጕድጓድ ነበረው፤ ወደዚያም ውስጥ ወረዱ፤
ባልዋም እያለቀሰ ከእርስዋ ጋር ሄደ፤ እስከ ብራቂም ድረስ ተከተላት። አበኔርም፥ “ሂድ፤ ተመለስ” አለው፤ እርሱም ተመለሰ።
ልብሱ ነውና፥ ዕርቃኑንም የሚሸፍንበት ይህ ብቻ ነውና፤ የሚተኛበትም ሌላ የለውምና፤ ወደ እኔም ቢጮኽ ፈጥኜ እሰማዋለሁ፤ መሓሪ ነኝና።
የሰማይ ዎፍ ቃልህን ያወጣዋልና፥ ክንፍ ያለውም ነገርህን ያወራዋልና በልብህ ዐሳብ እንኳን ቢሆን ንጉሥን አትሳደብ፥ በመኝታ ቤትህም ባለጠጋን አትሳደብ።
በዚህም በርግጥ ጽኑ ረኃብ ይመጣባችኋል፤ በተራባችሁም ጊዜ ትጨነቃላችሁ፤ በአለቆችና በመኳንንቱም ላይ ክፉ ትናገራላችሁ፤ ወደ ላይ ወደ ሰማይ ትመለከታላችሁ።
ፍልስጥኤማዊውም ዳዊትን፥ “በትርና ድንጋይ ይዘህ የምትመጣብኝ እኔ ውሻ ነኝን?” አለው። ዳዊትም፥ “የለም ከውሻ ትከፋለህ” አለው። ፍልስጥኤማዊውም ዳዊትን በአምላኮቹ ረገመው።