ያዕቆብም ራሔልን ወደዳት፤ ያዕቆብም ላባን እንዲህ አለው፥ “ስለ ታናሺቱ ልጅህ ስለ ራሔል ሰባት ዓመት እገዛልሃለሁ። ሚስት ትሆነኝ ዘንድ እርስዋን ስጠኝ” አለው።
2 ሳሙኤል 13:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ እንዲህ ሆነ፤ ለዳዊት ልጅ ለአቤሴሎም አንዲት የተዋበች እኅት ነበረችው፤ ስምዋም ትዕማር ነበረ፤ የዳዊትም ልጅ አምኖን ወደዳት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዳዊት ልጅ አቤሴሎም ትዕማር የምትባል ቈንጆ እኅት ነበረችው፤ እርሷንም የዳዊት ልጅ አምኖን ወደዳት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዳዊት ልጅ አቤሴሎም ትዕማር የምትባል ቆንጆ እኅት ነበረችው፤ የዳዊት ልጅ አምኖንም ወደዳት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዳዊት ልጅ አቤሴሎም ውብ የሆነች ትዕማር ተብላ የምትጠራ፥ ገና ባል ያላገባች እኅት ነበረችው፤ አምኖን ተብሎ የሚጠራው ከዳዊት ልጆች አንዱ ትዕማርን ወደዳት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚህም በኋላ እንዲህ ሆነ፥ ለዳዊት ልጅ ለአቤሴሎም አንዲት የተዋበች እኅት ነበረችው፥ ስምዋም ትዕማር ነበረ፥ የዳዊት ልጅ አምኖን ወደዳት። |
ያዕቆብም ራሔልን ወደዳት፤ ያዕቆብም ላባን እንዲህ አለው፥ “ስለ ታናሺቱ ልጅህ ስለ ራሔል ሰባት ዓመት እገዛልሃለሁ። ሚስት ትሆነኝ ዘንድ እርስዋን ስጠኝ” አለው።
ልቡናውም በያዕቆብ ልጅ በዲና ፍቅር ተነደፈ፤ ብላቴናዪቱንም ወደዳት፤ ልብዋንም ደስ በሚያሰኛት ነገር ተናገራት።
የእግዚአብሔር ልጆችም የሰውን ሴቶች ልጆች መልካሞች እንደሆኑ አዩ፤ ከመረጡአቸውም ሁሉ ሚስቶችን ለራሳቸው ወሰዱ።
እንዲህም ሆነ፤ ወደ ማታ ጊዜ ዳዊት ከምንጣፉ ተነሣ፤ በንጉሥም ቤት በሰገነት ላይ ተመላለሰ፤ በሰገነቱም ሳለ አንዲት ሴት ስትታጠብ አየ፤ ሴቲቱም እጅግ የተዋበች መልከ መልካም ነበረች።
ከዚያም በኋላ አምኖን ፈጽሞ ጠላት፤ አስቀድሞ ከአፈቀራት ፍቅር ይልቅ በኋላ የጠላት ጥል በለጠ። አምኖንም፥ “ተነሥተሽ ሂጂ” አላት።
አምኖንም ከእኅቱ ከትዕማር የተነሣ እስከሚታመም ድረስ እጅግ ተከዘ፤ ድንግልም ነበረችና አንዳች ነገር ያደርግባት ዘንድ በዐይኑ ፊት ጭንቅ ሆኖበት ነበር።
ለአቤሴሎምም ሦስት ወንዶች ልጆችና አንዲት ሴት ልጅ ተወለዱለት። የሴቲቱ ልጅም ስም ትዕማር ይባላል። ያችውም ሴት መልከ መልካም ነበረች፤ እርሷም የሰሎሞን ልጅ የሮብአም ሚስት ሆና አቢያን ወለደችለት።
ንጉሡም ሰሎሞን ሴቶችን ይወድ ነበር፥ ከባዕዳን ሕዝብም የፈርዖንን ልጅ፥ ሞዓባውያትንና አሞናውያትን፥ ሶርያውያትንና ሲዶናውያትን፥ ኤዶማውያትንና አሞሬዎናውያትንም፥ ኬጤዎናውያትንም፦ ሚስቶችን አገባ።