La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 1:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዳዊ​ትም ልብ​ሱን ቀደደ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በሩ ሰዎች ሁሉ ልብ​ሳ​ቸ​ውን ቀደዱ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ዳዊትና ዐብረውት የነበሩት ሰዎች ሁሉ ልብሳቸውን ቀደዱ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዚያም ዳዊት ልብሱን ቀደደ፤ ከእርሱም ጋር የነበሩ ሁሉ እንደዚሁ አደረጉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዳዊትም በሐዘን ልብሱን ቀደደ፤ ከእርሱም ጋር የነበሩ ተከታዮቹ ሁሉ እንደዚሁ አደረጉ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩ ሰዎች ሁሉ ልብሳቸውን ይዘው ቀደዱ።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 1:11
15 Referencias Cruzadas  

ሮቤ​ልም ወደ ጕድ​ጓዱ ተመ​ለሰ፤ እነ​ሆም፥ ዮሴ​ፍን ከጕ​ድ​ጓድ በአ​ጣው ጊዜ ልብ​ሱን ቀደደ።


ያዕ​ቆ​ብም ልብ​ሱን ቀደደ፤ በወ​ገ​ቡም ማቅ ታጥቆ ለልጁ ብዙ ቀን አለ​ቀሰ።


ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም ቀደዱ፤ ዓይ​በ​ታ​ቸ​ው​ንም በየ​አ​ህ​ዮ​ቻ​ቸው ጭነው ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ተመ​ለሱ።


ትዕ​ማ​ርም አመድ ወስዳ በራ​ስዋ ላይ ነሰ​ነ​ሰች፤ በላ​ይዋ የነ​በ​ረ​ው​ንም ብዙ ኅብር ያለ​ውን ልብ​ስ​ዋን ቀደ​ደ​ችው፤ እጅ​ዋ​ንም በራ​ስዋ ላይ ጭና እየ​ጮ​ኸች ሄደች።


ንጉ​ሡም ተነ​ሥቶ ልብ​ሱን ቀደደ፤ በም​ድር ላይም ወደቀ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ቁመው የነ​በሩ ብላ​ቴ​ኖቹ ሁሉ ልብ​ሳ​ቸ​ውን ቀደዱ።


ዳዊ​ትም ኢዮ​አ​ብ​ንና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ ሁሉ፥ “ልብ​ሳ​ች​ሁን ቅደዱ፤ ማቅም ልበሱ፤ በአ​በ​ኔ​ርም ፊት አል​ቅሱ” አላ​ቸው። ንጉ​ሡም ዳዊት ከቃ​ሬ​ዛው በኋላ ሄደ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ደብ​ዳ​ቤ​ውን ባነ​በበ ጊዜ ልብ​ሱን ቀድዶ፥ “ሰውን ከለ​ምጹ እፈ​ውስ ዘንድ ይህ ሰው ወደ እኔ መስ​ደዱ እኔ በውኑ ለመ​ግ​ደ​ልና ለማ​ዳን የም​ችል አም​ላክ ነኝን? ተመ​ል​ከቱ፥ የጠብ ምክ​ን​ያት እን​ደ​ሚ​ፈ​ል​ግ​ብኝ ተመ​ል​ከቱ” አለ።


በፊ​ቴም ራስ​ህን አዋ​ር​ደ​ሃ​ልና፥ በዚ​ህም ስፍራ በሚ​ኖ​ሩ​በት ላይ ቃሌን በሰ​ማህ ጊዜ ራስ​ህን አዋ​ር​ደ​ሃ​ልና፥ ልብ​ስ​ህ​ንም ቀድ​ደህ በፊቴ አል​ቅ​ሰ​ሃ​ልና እኔ ደግሞ ሰም​ቼ​ሃ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ይህ​ንም ነገር በሰ​ማሁ ጊዜ ልብ​ሴ​ንና መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ዬን ቀደ​ድሁ፤ አዘ​ን​ሁም፤ የራ​ሴ​ንና የጢ​ሜ​ንም ጠጕር ነጨሁ፤ ደን​ግ​ጬም ተቀ​መ​ጥሁ።


ንጉ​ሡም፥ ይህ​ንም ቃል ሁሉ የሰሙ አገ​ል​ጋ​ዮቹ ሁሉ አል​ደ​ነ​ገ​ጡም፤ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም አል​ቀ​ደ​ዱም።


ልባ​ች​ሁን እንጂ ልብ​ሳ​ች​ሁን አት​ቅ​ደዱ፤ አም​ላ​ካ​ች​ሁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሓ​ሪና ይቅር ባይ፥ ቍጣው የዘ​ገየ ምሕ​ረ​ቱም የበዛ፥ ለክ​ፋ​ትም የተ​ጸ​ጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመ​ለሱ።”


ሐዋ​ር​ያት በር​ና​ባ​ስና ጳው​ሎ​ስም በሰሙ ጊዜ፥ ልብ​ሳ​ቸ​ውን ቀደዱ፤ ፈጥ​ነ​ውም እየ​ጮኹ ወደ ሕዝቡ ሄዱ።


ደስ ከሚ​ለው ጋር ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ ከሚ​ያ​ለ​ቅ​ሰው ጋርም አል​ቅሱ።


ኢያ​ሱም ልብ​ሱን ቀደደ፤ እር​ሱና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ፊት እስከ ማታ ድረስ በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ተደፉ፤ በራ​ሳ​ቸ​ውም ላይ ትቢያ ነሰ​ነሱ።