በዚያም በደረስህ ጊዜ የናሜሲን ልጅ የኢዮሣፍጥን ልጅ ኢዩን ታገኘዋለህ፤ ገብተህም ከወንድሞቹ መካከል አስነሣው፤ ወደ ጓዳም አግባው።
2 ነገሥት 9:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በገባም ጊዜ፥ እነሆ፥ የሠራዊት አለቆች ተቀምጠው አገኘ፤ እርሱም፥ “አለቃ ሆይ፥ የምናገረው መልእክት አለኝ” አለ። ኢዩም፥ “ከማንኛችን ጋር ነው?” አለ። እርሱም፥ “አለቃ ሆይ፥ ከአንተ ጋር ነው” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ እንደ ደረሰም፣ የሰራዊቱ ጦር መኰንኖች በአንድነት ተቀምጠው ነበር፤ እርሱም “መኰንን ሆይ፤ ወደ አንተ ተልኬአለሁ” አለ። ኢዩም፣ “ለማንኛችን ነው?” ሲል ጠየቀ። እርሱም፣ “መኰንን ሆይ፤ ለአንተ ነው” ብሎ መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እዚያም እንደ ደረሰ የጦር መኰንኖች ተቀምጠው ሲወያዩ አግኝቶ “ጌታዬ ለአንተ የምሰጥህ መልእክት አለኝ” አለው። ኢዩም “ከእኛ መካከል ለማንኛችን ነው የምትናገረው?” ሲል ጠየቀው። ነቢዩም “የምናገረው ለአንተው ነው” ሲል መለሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እዚያም እንደ ደረሰ የጦር መኰንኖች ተቀምጠው ሲወያዩ አግኝቶ “ጌታዬ ለአንተ የምሰጥህ መልእክት አለኝ” አለው። ኢዩም “ከእኛ መካከል ለማንኛችን ነው የምትናገረው?” ሲል ጠየቀው። ነቢዩም “የምናገረው ለአንተው ነው” ሲል መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በገባም ጊዜ፥ እነሆ፥ የሠራዊት አለቆች ተቀምጠው ነበር፤ እርሱም “አለቃ ሆይ! ለአንተ መልእክት አለኝ፤” አለ። ኢዩም “ለማንኛችን ነው?” አለ። እርሱም “አለቃ ሆይ! ለአንተ ነው፤” አለ። |
በዚያም በደረስህ ጊዜ የናሜሲን ልጅ የኢዮሣፍጥን ልጅ ኢዩን ታገኘዋለህ፤ ገብተህም ከወንድሞቹ መካከል አስነሣው፤ ወደ ጓዳም አግባው።
ተነሥቶም ወደ ቤቱ ገባ፥ ዘይቱንም በራሱ ላይ አፍስሶ እንዲህ አለው፥ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእግዚአብሔር ሕዝብ በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባሁህ።
ዔግሎምም ከገልገል ከጣዖታቱ ቤት ተመለሰ። ናዖድም፥ “ንጉሥ ሆይ፥ ለብቻህ የምነግርህ የምሥጢር ነገር አለኝ” አለ፤ ዔግሎምም ሁሉ ከእርሱ ዘንድ እንዲወጣ አዘዘ፤ በእርሱም ዘንድ የቆሙት ሁሉ ወጡ ።