Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 3:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ዔግ​ሎ​ምም ከገ​ል​ገል ከጣ​ዖ​ታቱ ቤት ተመ​ለሰ። ናዖ​ድም፥ “ንጉሥ ሆይ፥ ለብ​ቻህ የም​ነ​ግ​ርህ የም​ሥ​ጢር ነገር አለኝ” አለ፤ ዔግ​ሎ​ምም ሁሉ ከእ​ርሱ ዘንድ እን​ዲ​ወጣ አዘዘ፤ በእ​ር​ሱም ዘንድ የቆ​ሙት ሁሉ ወጡ ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እርሱ ራሱ ግን ጌልገላ አጠገብ ድንጋዮች ተጠርበው ከሚወጡበት አካባቢ ሲደርስ ወደ ኋላ በመመለስ ወደ ንጉሡ ሄዶ፣ “ንጉሥ ሆይ፤ በምስጢር የምነግርህ ነገር አለኝ” አለው። ንጉሡም፣ “ጸጥታ” ሲል፤ አጠገቡ የነበሩት አገልጋዮች በሙሉ ትተዉት ወጡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 እርሱ ራሱ ግን ጌልጌላ አጠገብ ድንጋዮች ተጠርበው ከሚወጡበት አካባቢ ሲደርስ ወደ ኋላ በመመለስ ወደ ንጉሡ ሄዶ፥ “ንጉሥ ሆይ፤ በምስጢር የምነግርህ ነገር አለኝ” አለው። ንጉሡም፥ “ጸጥታ” ሲል፤ አጠገቡ የነበሩትአገልጋዮች በሙሉ ትተውት ወጡ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ኤሁድ ራሱ ግን በጌልገላ አጠገብ ወዳሉት ተጠርበው ወደ ተተከሉ የጣዖት ድንጋዮች ዞር ብሎ ቈየ፤ ወደ ዔግሎንም ተመልሶ “ንጉሥ ሆይ! በግል ለአንተ የምነግርህ አንድ ምሥጢር አለኝ” አለው። እርሱም “ዝም በል” አለው። ስለዚህም ንጉሡ ባለሟሎቹን “እስቲ አንድ ጊዜ ውጪ ቈዩልን!” አላቸው፥ እነርሱም በሙሉ ወጡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ናዖድ ግን በጌልገላ ከነበሩት ትክል ድንጋዮች ዘንድ ተመልሶ፦ ንጉሥ ሆይ፥ የምሥጢር ነገር አለኝ አለ፥ ንጉሡም፦ ዝም በል አለ፥ በዙሪያውም የቆሙት ሁሉ ወጡ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 3:19
8 Referencias Cruzadas  

ዮሴ​ፍም በፊቱ ሰዎች ሁሉ ቆመው ሳሉ ሊታ​ገሥ አል​ተ​ቻ​ለ​ውም፥ “ሰዎ​ቹ​ንም ሁሉ ከፊቴ አስ​ወ​ጡ​ልኝ” ብሎ ተና​ገረ፤ ዮሴፍ ለወ​ን​ድ​ሞቹ ራሱን በገ​ለጠ ጊዜ በእ​ርሱ ዘንድ የቆመ ማንም አል​ነ​በ​ረም።


ምጣ​ዱ​ንም ወስዳ በፊቱ ገለ​በ​ጠች፤ እርሱ ግን ይበላ ዘንድ እንቢ አለ። አም​ኖ​ንም፥ “ሰውን ሁሉ ከእኔ ዘንድ አስ​ወጡ” አለ፤ ሰውም ሁሉ ከእ​ርሱ ዘንድ ወጣ።


ኢያ​ሱም ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ውስጥ የወ​ሰ​ዱ​አ​ቸ​ውን እነ​ዚ​ያን ዐሥራ ሁለ​ቱን ድን​ጋ​ዮች በጌ​ል​ገላ አቆ​ማ​ቸው።


እጅ መን​ሻ​ው​ንም ማቅ​ረብ በጨ​ረሰ ጊዜ፥ እጅ መንሻ የተ​ሸ​ከ​ሙ​ትን ሰዎች አሰ​ና​በ​ታ​ቸው።


ናዖ​ድም ወደ እርሱ ገባ፤ እር​ሱም በበጋ ቤቱ ሰገ​ነት ለብ​ቻው ተቀ​ምጦ ነበር። ናዖ​ድም፥ “ንጉሥ ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​እ​ክት ለአ​ንተ አለኝ” አለው። ዔግ​ሎ​ምም ከዙ​ፋኑ ተነሣ፥ ቀረ​በ​ውም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos