Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መሳፍንት 3:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ኤሁድ ራሱ ግን በጌልገላ አጠገብ ወዳሉት ተጠርበው ወደ ተተከሉ የጣዖት ድንጋዮች ዞር ብሎ ቈየ፤ ወደ ዔግሎንም ተመልሶ “ንጉሥ ሆይ! በግል ለአንተ የምነግርህ አንድ ምሥጢር አለኝ” አለው። እርሱም “ዝም በል” አለው። ስለዚህም ንጉሡ ባለሟሎቹን “እስቲ አንድ ጊዜ ውጪ ቈዩልን!” አላቸው፥ እነርሱም በሙሉ ወጡ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እርሱ ራሱ ግን ጌልገላ አጠገብ ድንጋዮች ተጠርበው ከሚወጡበት አካባቢ ሲደርስ ወደ ኋላ በመመለስ ወደ ንጉሡ ሄዶ፣ “ንጉሥ ሆይ፤ በምስጢር የምነግርህ ነገር አለኝ” አለው። ንጉሡም፣ “ጸጥታ” ሲል፤ አጠገቡ የነበሩት አገልጋዮች በሙሉ ትተዉት ወጡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 እርሱ ራሱ ግን ጌልጌላ አጠገብ ድንጋዮች ተጠርበው ከሚወጡበት አካባቢ ሲደርስ ወደ ኋላ በመመለስ ወደ ንጉሡ ሄዶ፥ “ንጉሥ ሆይ፤ በምስጢር የምነግርህ ነገር አለኝ” አለው። ንጉሡም፥ “ጸጥታ” ሲል፤ አጠገቡ የነበሩትአገልጋዮች በሙሉ ትተውት ወጡ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ዔግ​ሎ​ምም ከገ​ል​ገል ከጣ​ዖ​ታቱ ቤት ተመ​ለሰ። ናዖ​ድም፥ “ንጉሥ ሆይ፥ ለብ​ቻህ የም​ነ​ግ​ርህ የም​ሥ​ጢር ነገር አለኝ” አለ፤ ዔግ​ሎ​ምም ሁሉ ከእ​ርሱ ዘንድ እን​ዲ​ወጣ አዘዘ፤ በእ​ር​ሱም ዘንድ የቆ​ሙት ሁሉ ወጡ ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ናዖድ ግን በጌልገላ ከነበሩት ትክል ድንጋዮች ዘንድ ተመልሶ፦ ንጉሥ ሆይ፥ የምሥጢር ነገር አለኝ አለ፥ ንጉሡም፦ ዝም በል አለ፥ በዙሪያውም የቆሙት ሁሉ ወጡ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 3:19
8 Referencias Cruzadas  

ዮሴፍ የናፍቆት ስሜቱን በአገልጋዮቹ ፊት መቈጣጠር ባለመቻሉ “ሁላችሁም ከዚህ ውጡ” ብሎ አዘዘ፤ ስለዚህ ዮሴፍ ማንነቱን ለወንድሞቹ በገለጠ ጊዜ ማንም የውጪ ሰው በአጠገቡ አልነበረም።


የጋገረችውንም እንጀራ ከምጣዱ አውጥታ እንዲበላ አቀረበችለት፤ እርሱ ግን መመገቡን እምቢ ብሎ “ሰዎቹን ሁሉ አስወጡልኝ” አለ፤ ሁሉም ወጡ፤


የአሕዛብ አምልኮ በሚፈጽሙባቸው ስፍራዎቻቸው እግዚአብሔርን አስቈጡት፤ በጣዖቶቻቸውም አስቀኑት።


በጌልገላም ኢያሱ ከዮርዳኖስ ወንዝ የተወሰዱትን ዐሥራ ሁለት ድንጋዮች አቁሞ፥


ኤሁድ ግብሩን ለንጉሡ ካቀረበ በኋላ ግብሩን ተሸክመው የነበሩትን ሰዎች ወደ ቤታቸው ተመልሰው እንዲሄዱ አደረገ፤


በዚያን ጊዜ ንጉሡ በጣራው ላይ ባለው ነፋሻ ክፍል ለብቻው ተቀምጦ ሳለ፥ ኤሁድ ወደ እርሱ ቀረብ ብሎ “ከእግዚአብሔር ለአንተ የተላከ መልእክት አለኝ” አለው፤ ንጉሡም ብድግ ብሎ ቆመ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios