መሳፍንት 3:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 እርሱ ራሱ ግን ጌልጌላ አጠገብ ድንጋዮች ተጠርበው ከሚወጡበት አካባቢ ሲደርስ ወደ ኋላ በመመለስ ወደ ንጉሡ ሄዶ፥ “ንጉሥ ሆይ፤ በምስጢር የምነግርህ ነገር አለኝ” አለው። ንጉሡም፥ “ጸጥታ” ሲል፤ አጠገቡ የነበሩትአገልጋዮች በሙሉ ትተውት ወጡ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 እርሱ ራሱ ግን ጌልገላ አጠገብ ድንጋዮች ተጠርበው ከሚወጡበት አካባቢ ሲደርስ ወደ ኋላ በመመለስ ወደ ንጉሡ ሄዶ፣ “ንጉሥ ሆይ፤ በምስጢር የምነግርህ ነገር አለኝ” አለው። ንጉሡም፣ “ጸጥታ” ሲል፤ አጠገቡ የነበሩት አገልጋዮች በሙሉ ትተዉት ወጡ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 ኤሁድ ራሱ ግን በጌልገላ አጠገብ ወዳሉት ተጠርበው ወደ ተተከሉ የጣዖት ድንጋዮች ዞር ብሎ ቈየ፤ ወደ ዔግሎንም ተመልሶ “ንጉሥ ሆይ! በግል ለአንተ የምነግርህ አንድ ምሥጢር አለኝ” አለው። እርሱም “ዝም በል” አለው። ስለዚህም ንጉሡ ባለሟሎቹን “እስቲ አንድ ጊዜ ውጪ ቈዩልን!” አላቸው፥ እነርሱም በሙሉ ወጡ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 ዔግሎምም ከገልገል ከጣዖታቱ ቤት ተመለሰ። ናዖድም፥ “ንጉሥ ሆይ፥ ለብቻህ የምነግርህ የምሥጢር ነገር አለኝ” አለ፤ ዔግሎምም ሁሉ ከእርሱ ዘንድ እንዲወጣ አዘዘ፤ በእርሱም ዘንድ የቆሙት ሁሉ ወጡ ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 ናዖድ ግን በጌልገላ ከነበሩት ትክል ድንጋዮች ዘንድ ተመልሶ፦ ንጉሥ ሆይ፥ የምሥጢር ነገር አለኝ አለ፥ ንጉሡም፦ ዝም በል አለ፥ በዙሪያውም የቆሙት ሁሉ ወጡ። Ver Capítulo |