La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 9:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ብላ​ቴ​ኖ​ቹም በሰ​ረ​ገ​ላው ጭነው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወሰ​ዱት፥ በዳ​ዊ​ትም ከተማ በመ​ቃ​ብሩ ቀበ​ሩት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አገልጋዮቹም በሠረገላ አድርገው ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት፤ በዳዊትም ከተማ ከአባቶቹ ጋራ በመቃብሩ ቀበሩት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ባለሟሎቹ የሆኑ ባለሥልጣኖችም ሬሳውን በሠረገላ ወደ ኢየሩሳሌም ወስደው በዳዊት ከተማ በሚገኘው የነገሥታት መካነ መቃብር ቀበሩት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ባለሟሎቹ የሆኑ ባለሥልጣኖችም ሬሳውን በሠረገላ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰደው በዳዊት ከተማ በሚገኘው የነገሥታት መካነ መቃብር ቀበሩት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ባሪያዎቹም በሠረገላው ጭነው ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት፤ በዳዊትም ከተማ በመቃብሩ ከአባቶቹ ጋር ቀበሩት።

Ver Capítulo



2 ነገሥት 9:28
9 Referencias Cruzadas  

ዳዊ​ትም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ተቀ​በረ።


አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም የኢ​ያ​ሙ​ሃት ልጅ ኢያ​ዜ​ክ​ርና የሳ​ሜር ልጅ ኢያ​ዛ​ብድ መቱት፤ ሞተም፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ቀበ​ሩት፤ ልጁም አሜ​ስ​ያስ በፋ​ን​ታው ነገሠ።


በዚ​ያም የነ​በ​ሩ​ትን የኮ​ረ​ብ​ታ​ውን መስ​ገ​ጃ​ዎች ካህ​ናት ሁሉ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ዎቹ ላይ ገደ​ላ​ቸው፥ የሰ​ዎ​ቹ​ንም አጥ​ንት በመ​ሠ​ዊ​ያ​ዎቹ ላይ አቃ​ጠለ። ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ተመ​ለሰ።


አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም በድ​ኑን በሰ​ረ​ገ​ላው አድ​ር​ገው ከመ​ጊዶ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አመ​ጡት፤ በመ​ቃ​ብ​ሩም ቀበ​ሩት። የሀ​ገ​ሩም ሰዎች የኢ​ዮ​ስ​ያ​ስን ልጅ ዮአ​ክ​ስን ወሰ​ዱት። ቀብ​ተ​ውም በአ​ባቱ ፋንታ አነ​ገ​ሡት።


ኢዮ​ራ​ምም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፥ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ተቀ​በረ፤ በፋ​ን​ታ​ውም ልጁ አካ​ዝ​ያስ ነገሠ።


አካ​ዝ​ያ​ስ​ንም ፈለ​ገው፤ በሰ​ማ​ር​ያም እየ​ታ​ከመ ሳለ አገ​ኙት፤ ወደ ኢዩም አመ​ጡት፤ እር​ሱም ገደ​ለው፦ እነ​ር​ሱም፥ “በፍ​ጹም ልብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የፈ​ለ​ገው የኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ ልጅ ነው” ብለው ቀበ​ሩት። ከአ​ካ​ዝ​ያ​ስም ቤት ማንም መን​ግ​ሥ​ትን ይይዝ ዘንድ የሚ​ችል አል​ነ​በ​ረም።


በፈ​ረ​ስም ጭነው አመ​ጡት፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ቀበ​ሩት።


ብላ​ቴ​ኖ​ቹም ከሰ​ረ​ገ​ላው አው​ር​ደው ለእ​ርሱ በነ​በ​ረው በሁ​ለ​ተ​ኛው ሰረ​ገላ ውስጥ አስ​ቀ​መ​ጡት፤ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አመ​ጡት፤ እር​ሱም በዚያ ሞተ፤ በአ​ባ​ቶ​ቹም መቃ​ብር ተቀ​በረ፤ ይሁ​ዳና ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሁሉ ለኢ​ዮ​ስ​ያስ አለ​ቀሱ።