በእስራኤልም ላይ ንጉሥ ይሆን ዘንድ የናሚሶን ልጅ ኢዩን ቅባው፤ በፋንታህም ነቢይ ይሆን ዘንድ የአቤልመሁላን ሰው የሣፋጥን ልጅ ኤልሳዕን ቅባው፤
2 ነገሥት 9:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም፥ “ዋሸኸን፤ ነገር ግን ንገረን” አሉት፤ ኢዩም፦ ለጌታው ልጆች፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባሁህ ብሎ እንዲህና እንዲህ ነገረኝ” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም፣ “ይህማ ትክክል አይደለም፤ ይልቅስ እውነቱን ንገረን” አሉት። ኢዩም እንዲህ አለ፤ “እርሱ የነገረኝማ ይህ ነው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ የእስራኤል ንጉሥ እንድትሆን ቀብቼሃለሁ።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም “ኧረ እኛ አናውቅም፤ ምን እንደ ተናገረ አስረዳን!” ሲሉ መለሱለት። ኢዩም፦ “‘በእስራኤል ላይ ተቀብተህ እንድትነግሥ እግዚአብሔር አዞአል’ አለኝ” ሲል አስረዳቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም “ኧረ እኛ አናውቅም፤ ምን እንደ ተናገረ አስረዳን!” ሲሉ መለሱለት። ኢዩም፦ “ ‘በእስራኤል ላይ ተቀብተህ እንድትነግሥ እግዚአብሔር አዞአል’ አለኝ” ሲል አስረዳቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም “ሐሰት ነው፤ ያለውን ንገረን፤” አሉት፤ እርሱም “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባሁህ፤’ ብሎ እንዲህ እንዲህ ነገረኝ፤” አላቸው። |
በእስራኤልም ላይ ንጉሥ ይሆን ዘንድ የናሚሶን ልጅ ኢዩን ቅባው፤ በፋንታህም ነቢይ ይሆን ዘንድ የአቤልመሁላን ሰው የሣፋጥን ልጅ ኤልሳዕን ቅባው፤
ኢዩም ወደ ጌታው ብላቴኖች ወጣ፤ እነርሱም፥ “ደኅና ነውን? ይህ እብድ ለምን ወደ አንተ መጣ?” አሉት። እርሱም፥ “ሰውዬው ፌዝ እንደሚናገር አታውቁምን?” አላቸው።
በሰሙም ጊዜ ሁሉም ፈጥነው ልብሳቸውን ወሰዱ፤ በሰገነቱ መውጫ እርከን ላይም ከእግሩ በታች አነጠፉት፥ መለከትም እየነፉ፥ “ኢዩ ነግሦአል” አሉ።
ሳሙኤልም የዘይቱን ቀንድ ወስዶ በራሱ ላይ አፈሰሰው፤ ሳመውም፤ እንዲህም አለው፥ “በሕዝቡ በእስራኤል ላይ ትነግሥ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶሃል፤ የእግዚአብሔርንም ሕዝብ ትገዛለህ፤ በዙሪያውም ካሉ ጠላቶቻቸው እጅ ታድናቸዋለህ። እግዚአብሔርም በርስቱ ላይ ትነግሥ ዘንድ እንደ ቀባህ ምልክቱ ይህ ነው።