የአሞንም ልጆች የዳዊት ወገኖች እንደ አፈሩ ባዩ ጊዜ፥ የአሞን ልጆች ልከው ከቤትሮዖብ ሶርያውያንና ከሱባ ሶርያውያን ሃያ ሺህ እግረኞችን፥ ከአማሌቅ ንጉሥም አንድ ሺህ ሰዎችን፥ ከአስጦብም ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎችን ቀጠሩ።
2 ነገሥት 7:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ለሶርያውያን የሰረገላ ድምፅ፥ የፈረስ ድምፅና የብዙ ጭፍራ ድምፅ አሰምቶአቸዋልና፥ እርስ በርሳቸው “እነሆ፥ የእስራኤል ንጉሥ ይከቡን ዘንድ የኬጤዎናውያንንና የግብፃውያንን ነገሥት ቀጥሮ አምጥቶብናል” ይባባሉ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህ የሆነበትም ምክንያት፣ እግዚአብሔር የሠረገሎችንና የፈረሶችን እንዲሁም የብዙ ሰራዊት ድምፅ ሶርያውያን እንዲሰሙ አድርጎ ስለ ነበር ነው፤ እርስ በርሳቸውም፣ “እነሆ፣ የእስራኤል ንጉሥ በእኛ ላይ አደጋ ለመጣል፣ የኬጢያውያንንና የግብጻውያንን ነገሥታት ቀጥሮ አምጥቶብናል” ተባባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም የሆነበት ምክንያት እግዚአብሔር ሶርያውያንን በፈረሶችና በሠረገሎች የታጀበ የብዙ ሠራዊት ግሥጋሤ የሚመስል ድምፅ አሰምቶአቸው ስለ ነበር ነው፤ ይኸውም ሶርያውያን እንዳሰቡት የእስራኤል ንጉሥ የሒታውያንና የግብጽ ነገሥታትን ከነሠራዊቶቻቸው ቀጥሮ አደጋ ሊጥልባቸው የመጣ መስሎአቸው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም የሆነበት ምክንያት እግዚአብሔር ሶርያውያንን በፈረሶችና በሠረገሎች የታጀበ የብዙ ሠራዊት ግሥጋሤ የሚመስል ድምፅ አሰምቶአቸው ስለ ነበር ነው፤ ይኸውም ሶርያውያን እንዳሰቡት የእስራኤል ንጉሥ የሒታውያንና የግብጽ ነገሥታትን ከነሠራዊቶቻቸው ቀጥሮ አደጋ ሊጥልባቸው የመጣ መስሎአቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ለሶርያውያን የሠረገላና የፈረስ የብዙም ጭፍራ ድምፅ አሰምቶ ነበር፤ እርስ በርሳቸውም “እነሆ፥ የእስራኤል ንጉሥ የኬጢያውያንና የግብጻውያንን ነገሥታት ቀጥሮ አምጥቶብናል፤” ይባባሉ ነበር። |
የአሞንም ልጆች የዳዊት ወገኖች እንደ አፈሩ ባዩ ጊዜ፥ የአሞን ልጆች ልከው ከቤትሮዖብ ሶርያውያንና ከሱባ ሶርያውያን ሃያ ሺህ እግረኞችን፥ ከአማሌቅ ንጉሥም አንድ ሺህ ሰዎችን፥ ከአስጦብም ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎችን ቀጠሩ።
በሾላውም ዛፍ ራስ ውስጥ የሽውሽውታ ድምፅ ስትሰማ፥ በዚያ ጊዜ እግዚአብሔር የፍልስጥኤማውያንን ጭፍራ ለመምታት በፊትህ ወጥቶ ይሆናልና በዚያ ጊዜ ፍጠን” አለው።
አንዱም ሰረገላ በስድስት መቶ፥ አንዱም ፈረስ በመቶ ኀምሳ ብር ከግብፅ ይወጣ ነበር። እንዲሁም ለኬጤዎናውያን ነገሥታትና ለሶርያ ነገሥታት ሁሉ በባሕሩ በኩል ያወጡላቸው ነበር።
አክዓብም ኤልያስን፥ “ጠላቴ ሆይ! አገኘኸኝን?” አለው። እርሱም እንዲህ ብሎ መለሰለት፥ “አግኝቼሃለሁ፤ ታስቈጣው ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አድርገሃልና እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
እነሆ፥ በላዩ መንፈስን እሰድዳለሁ፤ ወሬንም ይሰማል፤ ወደ ምድሩም ይመለሳል፤ በምድሩም በሰይፍ እንዲወድቅ አደርገዋለሁ በሉት።”
በጨለማም ወደ ሶርያውያን ሰፈር ይሄዱ ዘንድ ተነሡ፤ ወደ ሶርያውያንም ሰፈር መጀመሪያ ዳርቻ በመጡ ጊዜ፥ እነሆ፥ በዚያ ማንም ሰው አልነበረም።
ገንዘቡን በአራጣ የማያበድር፥ በንጹሑ ላይ መማለጃን የማይቀበል። እንዲህ የሚያደርግ ለዘለዓለም አይታወክም።
ርዳታ ለመፈለግ ወደ ግብፅ ለሚወርዱ፥ በፈረሶችና በሰረገሎችም ለሚታመኑ ወዮላቸው! ፈረሰኞቹ ብዙዎች ናቸውና፤ በእስራኤልም ቅዱስ አልታመኑምና፤ እግዚአብሔርንም አልፈለጉምና።
ከታናናሾቹ ከጌታዬ አገልጋዮች የሚያንሰውን የአንዱን ጭፍራ ፊት መመለስ እንዴት ትችላለህ? ስለ ሰረገሎችና ፈረሰኞች በግብፅ የሚታመኑ ለጌታዬ ባሮች ናቸው።
በእርስዋም ያሉ የተቀጠሩ ሠራተኞች በእርስዋ ተቀልበው እንደ ሰቡ ወይፈኖች ናቸው፤ የጥፋታቸው ቀንና የቅጣታቸው ጊዜ መጥቶባቸዋልና ተመለሱ፤ በአንድነትም ሸሹ፤ አልቆሙምም።
ሲሄዱም የክንፎቻቸው ድምፅ እንደ ብዙ ውኃ ድምፅ፥ ሁሉን እንደሚችል የአምላክም ድምፅ፥ እንደ ታላቅ ሠራዊትም ድምፅ ሆኖ ሰማሁ፤ ሲቆሙም ክንፎቻቸውን ይሰበስቡ ነበር።
የኪሩቤልም የክንፎቻቸው ድምፅ ሁሉን የሚችል አምላክ እንደሚናገረው ያለ ድምፅ እስከ ውጭው አደባባይ ድረስ በሩቅ ይሰማ ነበር።
በሰፈሩና በእርሻውም ድንጋጤ ሆነ፤ በሰፈሩ የተቀመጡ ሕዝብና የሚዋጉትም ሁሉ ተሸበሩ፤ መዋጋትም አልቻሉም፤ ምድሪቱም ተናወጠች፤ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ታላቅ ድንጋጤ መጣ።
ዳዊትም ኬጤያዊዉን አቤሜሌክንና የሶርህያን ልጅ የኢዮአብን ወንድም አቢሳን፥ “ወደ ሳኦል ወደ ሰፈሩ ከእኔ ጋር የሚገባ ማን ነው?” ብሎ ጠየቃቸው፤ አቢሳም፥ “እኔ ከአንተ ጋር እገባለሁ” አለ።