ከእነርሱም አንዱ፥ “አንተ ደግሞ ከእኛ ከአገልጋዮችህ ጋር ለመሄድ ና” አለ። ኤልሳዕም፥ “እሽ እኔም እመጣለሁ” አለ።
2 ነገሥት 6:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነርሱም ጋር ሄደ፤ ወደ ዮርዳኖስም በደረሱ ጊዜ እንጨት ቈረጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐብሯቸውም ሄደ። ወደ ዮርዳኖስም ሄደው ዛፎች መቍረጥ ጀመሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብረውም ሄዱ፤ ወደ ዮርዳኖስም በደረሱ ጊዜ ዛፍ የመቁረጥ ተግባራቸውን ጀመሩ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብረውም ሄዱ፤ ወደ ዮርዳኖስም በደረሱ ጊዜ ዛፍ የመቊረጥ ተግባራቸውን ጀመሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነርሱም ጋር ሄደ፤ ወደ ዮርዳኖስም በደረሱ ጊዜ እንጨት ቆረጡ። |
ከእነርሱም አንዱ፥ “አንተ ደግሞ ከእኛ ከአገልጋዮችህ ጋር ለመሄድ ና” አለ። ኤልሳዕም፥ “እሽ እኔም እመጣለሁ” አለ።
ከእነርሱም አንዱ ዛፉን ሲቈርጥ የምሳሩ ብረት ወልቆ ወደ ውኃው ውስጥ ወደቀ፤ እርሱም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ወየው! ወየው! የተዋስሁት ነበር” ብሎ ጮኸ።
ሰው ከባልንጀራው ጋር እንጨት ሊለቅም ወደ ዱር ቢሄድ፥ ዛፉንም ሲቈርጥ ምሳሩ ከእጁ ቢወድቅ፥ ብረቱም ከእጄታው ቢወልቅ፥ በባልንጀራውም ላይ ቢወድቅና ቢገድለው፥ ከእነዚህ ከተሞች በአንዲቱ ተማጥኖ በሕይወት ይኖራል፤