በኢዮአብ ራስ ላይና በአባቱ ቤት ሁሉ ላይ ይምጣበት፤ በኢዮአብም ቤት ፈሳሽ ነገር ያለበት ወይም ለምጻም ወይም አንካሳ ወይም በሰይፍ የሚወድቅ ወይም እንጀራ የሌለው ሰው አይታጣ።”
2 ነገሥት 5:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን የንዕማን ለምጽ በአንተና በዘርህ ላይ፥ ለዘለዓለም ይመለስ” አለው። እንደ በረዶም ለምጻም ሆኖ ከእርሱ ዘንድ ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ የንዕማን የቈዳ በሽታ በአንተ ላይ ይጣበቃል፤ ለዘላለምም ወደ ዘርህ ይተላለፋል።” ከዚያም ግያዝ ከኤልሳዕ ፊት ወጣ፤ እንደ በረዶ እስኪነጣም ድረስ ለምጻም ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም የተነሣ እነሆ፥ የንዕማን የቆዳ በሽታ ወደ አንተ ይተላለፋል፤ አንተና ዘሮችህ ለዘለዓለም ከዚያ በሽታ አትነጹም!” አለው። ግያዝም ወጥቶ ሲሄድ፥ ያ የቆዳ በሽታ ስለ ተጋባበት ገላው እንደ በረዶ ነጭ ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም የተነሣ እነሆ፥ የንዕማን የቆዳ በሽታ ወደ አንተ ይተላለፋል፤ አንተና ዘሮችህ ለዘለዓለም ከዚያ በሽታ አትነጹም!” አለው። ግያዝም ወጥቶ ሲሄድ፥ ያ የቆዳ በሽታ ስለ ተጋባበት ገላው እንደ በረዶ ነጭ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህስ የንዕማን ለምጽ በአንተ ላይ በዘርህም ላይ ለዘላለም ይጣበቃል፤” አለው። እንደ በረዶም ለምጻም ሆኖ ከእርሱ ዘንድ ወጣ። |
በኢዮአብ ራስ ላይና በአባቱ ቤት ሁሉ ላይ ይምጣበት፤ በኢዮአብም ቤት ፈሳሽ ነገር ያለበት ወይም ለምጻም ወይም አንካሳ ወይም በሰይፍ የሚወድቅ ወይም እንጀራ የሌለው ሰው አይታጣ።”
እግዚአብሔርም ንጉሡን በደዌ ዳሰሰው፤ እስከሚሞትበትም ቀን ለምጻም ሆነ፤ በተለየ ቤትም ይቀመጥ ነበር፤ የንጉሡም ልጅ ኢዮአታም በንጉሡ ቤት ላይ ሠልጥኖ ለሀገሩ ሕዝብ ይፈርድ ነበር።
የሶርያ ንጉሥ ሠራዊት አለቃ ንዕማንም እግዚአብሔር በእርሱ እጅ ለሶርያ ደኅንነትን ስለ ሰጠ፥ በጌታው ዘንድ ታላቅና ክቡር ሰው ነበረ፤ ሰውዬውም ጽኑዕ፥ ኀያል ነበረ፤ ነገር ግን ለምጻም ነበረ።
አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና። በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኀጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤
ዳግመኛም እግዚአብሔር፥ “እጅህን ወደ ብብትህ አግባ አለው።” እጁንም ወደ ብብቱ አገባት፤ “እጅህንም ከብብትህ አውጣ” አለው፤ እጁንም ከብብቱ አወጣ፤ እጁም ለምጽ ሆነች።
ዐመፅን ለምን ተከላችሁ? ኀጢአትንስ ለምን አጨዳችሁ፤ የሐሰትንም ፍሬ በልታችኋል፤ በሠረገሎችህና በሠራዊትህ ብዛት ታምነሃል።
ካህኑ ያየዋል፤ እነሆም፥ በቋቁቻው ጠጕሩ ተለውጦ ቢነጣ፥ ወደ ቆዳውም ውስጥ ቢጠልቅ፥ ለምጽ ነው፤ ከተቃጠለውም ስፍራ ወጥቶአል፤ ካህኑም፦ ‘ርኩስ ነው’ ይለዋል፤ የለምጽ ደዌ ነውና።
ደመናውም ከድንኳኑ ተነሣ፤ እነሆም፥ ማርያም ለምጻም ሆነች፤ እንደ በረዶም ነጭ ሆነች፤ አሮንም ማርያምን ተመለከተ፤ እነሆም፥ ለምጻም ሆና ነበር።
ኢያሱም፥ “ለምን አጠፋኸን? ዛሬ እንዳጠፋኸን እግዚአብሔር ዛሬ ያጥፋህ” አለው፤ እስራኤልም ሁሉ በድንጋይ ወገሩት፤ በእሳትም አቃጠሉት፤ በድንጋይም ወገሩአቸው።