ያችም ሴት፥ “ለመግደል ባለ ደሞች እንዳይበዙ፤ ልጄንም እንዳይገድሉብኝ ንጉሥ ፈጣሪው እግዚአብሔርን ያስብ” አለች። እርሱም፥ “የልጅሽስ አንዲት የራሱ ጠጕር በምድር ላይ እንዳትወድቅ ሕያው እግዚአብሔርን” አላት።
2 ነገሥት 25:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጎዶልያም፥ “ከከለዳውያን ሎሌዎች የተነሣ አትፍሩ፤ በሀገሩ ተቀመጡ፤ ለባቢሎንም ንጉሥ ተገዙ፤ መልካምም ይሆንላችኋል” ብሎ ለእነርሱና ለሰዎቻቸው ማለላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጎዶልያስም፣ “የባቢሎናውያንን ሹማምት አትፍሩ፤ እዚሁ አገር ኑሩ፤ የባቢሎንን ንጉሥ አገልግሉ፤ ሁሉም ነገር ይሳካላችኋል” ሲል ይህንኑ በቃለ መሐላ አረጋገጠላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ገዳልያም እነርሱንና ወታደሮቻቸውን እንዲህ አላቸው፤ “ከባቢሎናውያን ባለ ሥልጣኖች የተነሣ ምንም ዓይነት ፍርሀት ሊያድርባችሁ እንደማይገባ ቃል እገባላችኋለሁ፤ በዚህች ምድር ኑሮአችሁን መሥርቱ፤ ለባቢሎን ንጉሥ ገብሩ፤ ይህን ብታደርጉ ሁሉ ነገር ይቃናላችኋል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ገዳልያም እነርሱንና ወታደሮቻቸውን እንዲህ አላቸው፤ “ከባቢሎናውያን ባለሥልጣኖች የተነሣ ምንም ዐይነት ፍርሀት ሊያድርባችሁ እንደማይገባ ቃል እገባላችኋለሁ፤ በዚህች ምድር ኑሮአችሁን መሥርቱ፤ ለባቢሎን ንጉሥ ገብሩ፤ ይህን ብታደርጉ ሁሉ ነገር ይቃናላችኋል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጎዶልያስም “ከከለዳውያን ሎሌዎች የተነሣ አትፍሩ፤ በአገሩ ተቀመጡ፤ ለባቢሎንም ንጉሥ ተገዙ፤ መልካምም ይሆንላችኋል፤” ብሎ ለእነርሱና ለሰዎቻቸው ማለላቸው። |
ያችም ሴት፥ “ለመግደል ባለ ደሞች እንዳይበዙ፤ ልጄንም እንዳይገድሉብኝ ንጉሥ ፈጣሪው እግዚአብሔርን ያስብ” አለች። እርሱም፥ “የልጅሽስ አንዲት የራሱ ጠጕር በምድር ላይ እንዳትወድቅ ሕያው እግዚአብሔርን” አላት።
የሠራዊቱም አለቆች ሁሉ ሰዎቻቸውም፥ የናታንዩ ልጅ እስማኤል፥ የቃሬያን ልጅ ዮሐናን፥ የነጦፋዊውም የተንሑሜት ልጅ ሴሪያ፥ የማዕካታዊው ልጅ አዛንያ፥ ሰዎቻቸውም የባቢሎን ንጉሥ ጎዶልያን እንደ ሾመው በሰሙ ጊዜ ወደ ጎዶልያ ወደ መሴፋ መጡ።
በሰባተኛው ወር ግን የመንግሥት ዘር የነበረ የኤልሴማ ልጅ የናታንዩ ልጅ እስማኤል መጣ፤ ከእርሱም ጋር ዐሥር ሰዎች ነበሩ፤ ጎዶልያንም መታው፤ ሞተም፤ ከእርሱም ጋር በመሴፋ የነበሩትን አይሁድንና ከለዳውያንንም ገደላቸው።
ወንዶችንና ሴቶችን፥ ሕፃናቱንም፥ የንጉሡንም ሴቶች ልጆች፥ የአዛዦችም አለቃ ናቡዛርዳን ከሳፋን ልጅ ከአኪቃም ልጅ ከጎዶልያስ ጋር የተዋቸውን ሰዎች ሁሉ፥ ነቢዩ ኤርምያስንና የኔርዩን ልጅ ባሮክንም ወሰዱ።