የእግዚአብሔርም ሰው በመሠዊያው ላይ፥ “መሠዊያ ሆይ፥ መሠዊያ ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ስሙ ኢዮስያስ የሚባል ልጅ ለዳዊት ቤት ይወለዳል፤ ዕጣንም የሚያጥኑብህን የኮረብታ መስገጃዎቹን ካህናት ይሠዋብሃል፤ የሰዎቹንም አጥንት ያቃጥልብሃል” ብሎ በእግዚአብሔር ቃል ጠራ።
2 ነገሥት 22:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮስያስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የስምንት ዓመት ልጅ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ሠላሳ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም ከባሱሮት የሆነ የአዳያ ልጅ ይዲያ ነበረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮስያስ በነገሠ ጊዜ፣ ዕድሜው ስምንት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ሠላሳ አንድ ዓመት ገዛ። እናቱም የቦጽቃት አገር ሰው የአዳያ ልጅ ይዲዳ ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮስያስ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ገና ስምንት ዓመት ነበር፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ሠላሳ አንድ ዓመት ገዛ፤ እናቱም ይዲዳ ተብላ የምትጠራ የቦጽቃት ከተማ ተወላጅ የሆነው የዐዳያ ልጅ ነበረች፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮስያስ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ገና ስምንት ዓመት ነበር፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ሠላሳ አንድ ዓመት ገዛ፤ እናቱም ይዲዳ ተብላ የምትጠራ የቦጽቃት ከተማ ተወላጅ የሆነው የዐዳያ ልጅ ነበረች፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮስያስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የስምንት ዓመት ልጅ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ሠላሳ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም ከባሱሮት የሆነ የአዳያ ልጅ ይዲዳ ነበረች። |
የእግዚአብሔርም ሰው በመሠዊያው ላይ፥ “መሠዊያ ሆይ፥ መሠዊያ ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ስሙ ኢዮስያስ የሚባል ልጅ ለዳዊት ቤት ይወለዳል፤ ዕጣንም የሚያጥኑብህን የኮረብታ መስገጃዎቹን ካህናት ይሠዋብሃል፤ የሰዎቹንም አጥንት ያቃጥልብሃል” ብሎ በእግዚአብሔር ቃል ጠራ።
ምናሴም በነገሠ ጊዜ ዐሥራ ሁለት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ኀምሳ አምስት ዓመት ነገሠ፤ የእናቱም ስም ሐፍሴባ ነበረ።
የሀገሩ ሕዝብ ግን በንጉሡ በአሞጽ ላይ ያሴሩትን ሁሉ ገደሉ፤ የሀገሩም ሕዝብ ልጁን ኢዮስያስን በእርሱ ፋንታ አነገሡት።
በይሁዳ ንጉሥ በአሞጽ ልጅ በኢዮስያስ ዘመን ወደ ሕዝቅያስ ልጅ ወደ አማርያ ልጅ ወደ ጎዶልያስ ልጅ ወደ ኵሲ ልጅ ወደ ሶፎንያስ የመጣ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው።