2 ነገሥት 20:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቅያስም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊት ከተማም ቀበሩት። ልጁ ምናሴም በእርሱ ፋንታ ነገሠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቅያስም ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ ልጁ ምናሴም በእግሩ ተተካ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቅያስም ሞተ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ምናሴ ነገሠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቅያስም ሞተ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ምናሴ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቅያስም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ ልጁም ምናሴ በእርሱ ፋንታ ነገሠ። |
ምናሴም በነገሠ ጊዜ ዐሥራ ሁለት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ኀምሳ አምስት ዓመት ነገሠ፤ የእናቱም ስም ሐፍሴባ ነበረ።
ዖዝያንም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ ለምጻም ነው ብለዋልና የነገሥታቱ መቃብር ባልሆነ እርሻ ውስጥ ቀበሩት፤ ልጁም ኢዮአታም በእርሱ ፋንታ ነገሠ።
ሕዝቅያስም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ልጆች መቃብር በላይኛው ክፍል ቀበሩት፤ በይሁዳና በኢየሩሳሌም የሚኖሩትም ሁሉ በሞቱ አከበሩት። ልጁም ምናሴ በእርሱ ፋንታ ነገሠ።