2 ነገሥት 19:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቍጣህና ትዕቢትህ ወደ ጆሮዬ ደርሶአልና ስለዚህ ስናጋዬን በአፍንጫህ፥ ልጓሜንም በከንፈርህ አደርጋለሁ፤ በመጣህበት መንገድም እመልስሃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእኔ ላይ በቍጣ ስለ ተነሣሣህ፣ እብሪትህም ወደ ጆሮዬ ስለ ደረሰ፣ ስናጋዬን በአፍንጫህ አደርጋለሁ፤ ልጓሜን በአፍህ አስገባለሁ፤ በመጣህበትም መንገድ እንድትመለስ አደርግሃለሁ።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእኔ ላይ ያለው ተቃውሞህና ትዕቢትህ ወደ ጆሮዬ ደርሶአል፤ በአፍንጫህ ስናጋ፥ በአፍህ ልጓም አድርጌ፥ በመጣህበት መንገድ እመልስሃለሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእኔ ላይ ያለው ተቃውሞህና ትዕቢትህ ወደ ጆሮዬ ደርሶአል፤ በአፍንጫህ ስናጋ፥ በአፍህ ልጓም አድርጌ፥ በመጣህበት መንገድ እመልስሃለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቍጣህና ትዕቢትህ ወደ ጆሮዬ ደርሶአልና ስለዚህ ስናጋዬን በአፍንጫህ፥ ልጓሜንም በከንፈርህ አደርጋለሁ፤ በመጣህበትም መንገድ እመልስሃለሁ። |
እነሆ፥ በላዩ መንፈስን እሰድዳለሁ፤ ወሬንም ይሰማል፤ ወደ ምድሩም ይመለሳል፤ በምድሩም በሰይፍ እንዲወድቅ አደርገዋለሁ በሉት።”
እስትንፋሱም አሕዛብን ስለ ከንቱ ስሕተታቸው ሊከፋፍላቸው በሸለቆ እንደሚያጥለቀልቅ፥ እስከ አንገትም እንደሚደርስና እንደሚከፋፍል ውኃ ይጐርፋል፤ ስሕተታቸውም ይከተላቸዋል፤ ይወስዳቸዋልም።
በሰንሰለትም አስረው በቀፎ ውስጥ አኖሩት፤ ወደ ባቢሎንም ንጉሥ አመጡት፤ ድምፁም በእስራኤል ተራሮች ላይ ከዚያ ወዲያ እንዳይሰማ ወደ ግዞት ቤት አገቡት።
በመንጋጋዎችህ መቃጥን አገባብሃለሁ፤ የወንዞችህንም ዓሦች ሁሉ ወደ ቅርፊትህ አጣብቃለሁ፤ ከወንዞችህም መካከል አወጣሃለሁ፤ የወንዞችህም ዓሦች ሁሉ ወደ ቅርፊትህ ይጣበቃሉ።
እመልስህማለሁ፤ በመንጋጋህም ልጓም አገባብሃለሁ፤ አንተንና ሠራዊትህን ሁሉ፥ ፈረሶችንና ፈረሰኞችን፥ የጦር ልብስ የለበሱትን ሁሉ፥ ጋሻና ራስ ቍርን፥ ሰይፍንም የያዙትን ሁሉ አወጣለሁ።
ጌታ አግዚአብሔር፥ “እናንተን በሰልፍ ዕቃ፥ ቅሬታችሁንም በመቃጥን የሚወስዱበት ቀን እነሆ በላያችሁ ይመጣል” ብሎ በቅዱስነቱ ምሎአል።
“እናንተ አንገታችሁ የደነደነ፥ ልባችሁም የተደፈነ፥ ጆሮአችሁም የደነቈረ፥ እንደ አባቶቻችሁ መንፈስ ቅዱስን ዘወትር ትቃወማላችሁ።