ዳዊትም ኢዮአብንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሕዝብ ሁሉ፥ “ልብሳችሁን ቅደዱ፤ ማቅም ልበሱ፤ በአበኔርም ፊት አልቅሱ” አላቸው። ንጉሡም ዳዊት ከቃሬዛው በኋላ ሄደ።
2 ነገሥት 19:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቤቱንም አዛዥ ኤልያቄምን ጸሓፊውንም ሳምናስን የካህናቱንም አለቆች ማቅ ለብሰው ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ነቢዩ ኢሳይያስ ይሄዱ ዘንድ ላካቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የቤተ መንግሥቱን አዛዥ ኤልያቄምን፣ ጸሓፊውን ሳምናስንና ከካህናቱ ዋና ዋናዎቹን ማቅ ለብሰው ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ነቢዩ ኢሳይያስ እንዲሄዱ ላካቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወዲያውም የቤተ መንግሥቱ ኃላፊ የሆነውን ኤልያቄምን፥ የቤተ መንግሥቱን ጸሐፊ ሼብናንና ሽማግሌዎች ካህናትን ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ነቢዩ ኢሳይያስ ላከ፤ እነርሱም ራሳቸው ማቅ ለብሰው ነበር፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወዲያውም የቤተ መንግሥቱ ኀላፊ የሆነውን ኤልያቄምን፥ የቤተ መንግሥቱን ጸሐፊ ሼብናንና ሽማግሌዎች ካህናትን ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ነቢዩ ኢሳይያስ ላከ፤ እነርሱም ራሳቸው ማቅ ለብሰው ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቤቱንም አዛዥ ኤልያቄምን ጸሐፊውንም ሳምናስን የካህናቱንም ሽማግሌዎች ማቅ ለብሰው ወደ ነቢዩ ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ኢሳይያስ ይሄዱ ዘንድ ላካቸው። |
ዳዊትም ኢዮአብንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሕዝብ ሁሉ፥ “ልብሳችሁን ቅደዱ፤ ማቅም ልበሱ፤ በአበኔርም ፊት አልቅሱ” አላቸው። ንጉሡም ዳዊት ከቃሬዛው በኋላ ሄደ።
በሣጥኑም ውስጥ የተገኘው ወርቅ ብዙ እንደ ሆነ ባዩ ጊዜ የንጉሡ ጸሓፊና የካህናቱ አለቃ ይመጡ ነበር፤ በእግዚአብሔርም ቤት የተገኘውን ገንዘብ ሁሉ ቈጥረው በከረጢት ውስጥ ያኖሩት ነበር።
ሕዝቅያስንም ጠሩ፤ የቤቱም አዛዥ የኬልቅዩ ልጅ ኤልያቄም ጸሓፊውም ሳምናስ ታሪክ ጸሓፊውም የአሳፍ ልጅ ዮአስ ወደ እነርሱ ወጡ።
እነርሱም አሉት፥ “ሕዝቅያስ እንዲህ ይላል፦ ይህ ቀን የመከራና የተግሣጽ የዘለፋም ቀን ነው፤ ልጆች የሚወለዱበት ጊዜ ደርሶአል፤ እናትም ለማማጥ ኀይል የላትም።
በይሁዳ ነገሥታት በዖዝያንና በኢዮአታም፥ በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው የአሞጽ ልጅ የኢሳይያስ ራእይ።
እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ “ሂድ፤ የሸክላ ሠሪ የሠራውን ገምቦ ግዛ፤ ከሕዝቡም ሽማግሌዎችና ከካህናት ሽማግሌዎች ከአንተ ጋር ውሰድ፤
በምድረ በዳ የሚጮኽ የአዋጅ ነጋሪ ድምፅ በነቢዩ በኢሳይያስ መጽሐፍ ቃል እንደ ተጻፈ፥ እንዲህ ሲል፥ “የእግዚአብሔርን መንገድ ጥረጉ፤ ጥርጊያውንም አስተካክሉ።