2 ነገሥት 14:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጋትሔፌር በነበረው በአማቴ ልጅ በባሪያው በነቢዩ በዮናስ አፍ እንደ ተናገረው እንደ እስራኤል አምላክ እንደ እግዚአብሔር ቃል የእስራኤልን ድንበር ከሔማት መግቢያ ጀምሮ እስከ ዓረባ ባሕር ድረስ መለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር በጋትሔፌር ነቢይ፣ በአማቴ ልጅ በባሪያው በዮናስ አማካይነት እንደ ተናገረው፣ ከሐማት መተላለፊያ አንሥቶ እስከ ሙት ባሕር ድረስ የነበረውን የእስራኤልን ድንበር አስመለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀድሞ የእስራኤል ይዞታ የነበረውን በስተ ሰሜን ከሐማት መተላለፊያ ጀምሮ በስተ ደቡብ እስከ ሙት ባሕር የሚገኘውን ግዛት ሁሉ ድል ነሥቶ እንደገና አስመለሰ፤ ይህም ሁሉ የተፈጸመው በጋትሔፌር ተወላጅ አገልጋይ በሆነው በአሚታይ ልጅ በነቢዩ ዮናስ አማካይነት የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር በሰጠው የተስፋ ቃል መሠረት ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀድሞ የእስራኤል ይዞታ የነበረውን በስተ ሰሜን ከሐማት መተላለፊያ ጀምሮ በስተ ደቡብ እስከ ሙት ባሕር የሚገኘውን ግዛት ሁሉ ድል ነሥቶ እንደገና አስመለሰ፤ ይህም ሁሉ የተፈጸመው በጋትሔፌር ተወላጅ አገልጋይ በሆነው በአሚታይ ልጅ በነቢዩ ዮናስ አማካይነት የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር በሰጠው የተስፋ ቃል መሠረት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጋትሔፌር በነበረው በአማቴ ልጅ በባሪያው በነቢዩ በዮናስ እንደ ተናገረው እንደ እስራኤል አምላክ እንደ እግዚአብሔር ቃል የእስራኤልን ድንበር ከሐማት መግቢያ ጀምሮ እስከ ዓረባ ባሕር ድረስ መለሰ። |
በዚያም ዘመን ሰሎሞን፥ ከእርሱም ጋር እስራኤል ሁሉ ከኤማት መግቢያ ጀምሮ እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ ያለው ታላቅ ጉባኤ፥ እርሱ በሠራው ቤት ውስጥ በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት እየበሉና እየጠጡ፥ ደስታም እያደረጉ ሰባት ቀን በዓሉን አከበሩ።
አዛሄልም ከአባቱ ከኢዮአካዝ እጅ በሰልፍ የወሰዳቸውን ከተሞች የኢዮአካዝ ልጅ ዮአስ መልሶ ከአዛሄል ልጅ ከወልደ አዴር እጅ ወሰደ። ዮአስም ሦስት ጊዜ መታው፤ የእስራኤልንም ከተሞች መለሰ።
እግዚአብሔርም ለእስራኤል ታዳጊን ሰጠ፤ ከሶርያውያንም እጅ ዳኑ፤ የእስራኤልም ልጆች እንደ ቀድሞው ጊዜ በድንኳናቸው ተቀመጡ።
በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ ነገር አደረገ እስራኤልንም ካሳታቸው ከናባጥ ልጅ ከኢዮርብዓም ኀጢአት ሁሉ አልራቀም።
በሰይፍ ትወድቃላችሁ፤ በእስራኤልም ተራሮች እፈርድባችኋለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
“የእስራኤል ቤት ሆይ እነሆ እኔ የሚያስጨንቋችሁን ሕዝብ አስነሣባችኋለሁ፥” ይላል የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር፤ እነርሱም ከሐማት መግቢያ ጀምረው እስከ ዐረባ ወንዝ ድረስ ትገቡ ዘንድ አይፈቅዱላችሁም።
ከመካናራ ወሰን ከፈስጋ ተራራ በታች ወደ ምሥራቅ እስከ ዓረባ ባሕር እርሱም የጨው ባሕር ድረስ ዓረባን፥ ዮርዳኖስንም ሰጠኋቸው።