La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 14:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​አስ ልጅ በአ​ሜ​ስ​ያስ በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ የዮ​አስ ልጅ ኢዮ​ር​ብ​ዓም በሰ​ማ​ርያ መን​ገሥ ጀመረ፤ አርባ አንድ ዓመ​ትም ነገሠ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የኢዮአስ ልጅ አሜስያስ በይሁዳ በነገሠ በዐሥራ ዐምስተኛው ዓመት፣ የእስራኤል ንጉሥ የዮአስ ልጅ ኢዮርብዓም በሰማርያ ነገሠ፤ አርባ አንድ ዓመትም ገዛ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የኢዮአስ ልጅ አሜስያስ በይሁዳ በነገሠ በዐሥራ አምስተኛው ዓመት የዮአስ ልጅ ኢዮርብዓም በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ እርሱም መኖሪያውን በሰማርያ አድርጎ አርባ አንድ ዓመት ገዛ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የኢዮአስ ልጅ አሜስያስ በይሁዳ በነገሠ በዐሥራ አምስተኛው ዓመት የዮአስ ልጅ ኢዮርብዓም በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ አርሱም መኖሪያውን በሰማርያ አድርጎ አርባ አንድ ዓመት ገዛ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በይሁዳ ንጉሥ በኢዮአስ ልጅ በአሜስያስ በዐሥራ አምስተኛው ዓመት የእስራኤል ንጉሥ የዮአስ ልጅ ኢዮርብዓም በሰማርያ መንገሥ ጀመረ፤ አርባ አንድ ዓመትም ነገሠ።

Ver Capítulo



2 ነገሥት 14:23
13 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢዩን፥ “በፊቴ ቅን ነገር አድ​ር​ገ​ሃ​ልና፥ በል​ቤም ያለ​ውን ሁሉ በአ​ክ​አብ ቤት ላይ አድ​ር​ገ​ሃ​ልና ልጆ​ችህ እስከ አራት ትው​ልድ ድረስ በእ​ስ​ራ​ኤል ዙፋን ላይ ይቀ​መ​ጣሉ” አለው።


ዮአ​ስም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም በዙ​ፋኑ ላይ ተቀ​መጠ፤ ዮአ​ስም በሰ​ማ​ርያ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት ጋር ተቀ​በረ።


በእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ በኢ​ዮ​አ​ካዝ ልጅ በዮ​አስ በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓመት የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​አስ ልጅ አሜ​ስ​ያስ ነገሠ።


የቀ​ረ​ውም ያደ​ረ​ገው የዮ​አስ ነገር፥ ኀይ​ሉም፥ ከይ​ሁ​ዳም ንጉሥ ከአ​ሜ​ስ​ያስ ጋር እንደ ተዋጋ፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?


ዮአ​ስም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በሰ​ማ​ር​ያም ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት ጋር ተቀ​በረ፤ ልጁም ኢዮ​ር​ብ​ዓም በፋ​ን​ታው ነገሠ።


ንጉ​ሡም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ከአ​ን​ቀ​ላፋ በኋላ፥ ኤላ​ትን ሠርቶ ወደ ይሁዳ መለ​ሳት።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ ነገር አደ​ረገ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ካሳ​ታ​ቸው ከና​ባጥ ልጅ ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አት ሁሉ አል​ራ​ቀም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ዘር ከሰ​ማይ በታች ይደ​መ​ስስ ዘንድ አል​ተ​ና​ገ​ረም፤ ነገር ግን በዮ​አስ ልጅ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም እጅ አዳ​ና​ቸው።


በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም በሃያ ሰባ​ተ​ኛው ዓመት የይ​ሁዳ ንጉሥ የአ​ሜ​ስ​ያስ ልጅ ዓዛ​ር​ያስ ነገሠ።


እነ​ዚህ ሁሉ በት​ው​ል​ዶ​ቻ​ቸው በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​አ​ታም ዘመ​ንና በእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ዘመን ተቈ​ጠሩ።


በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት በዖ​ዝ​ያ​ንና በኢ​ዮ​አ​ታም በአ​ካ​ዝና በሕ​ዝ​ቅ​ያ​ስም ዘመን በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በኢ​ዮ​አስ ልጅ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ዘመን ወደ ብኤሪ ልጅ ወደ ሆሴዕ የመጣ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ይህ ነው።


በቴ​ቁሔ በላም ጠባ​ቂ​ዎች መካ​ከል የነ​በረ አሞጽ በይ​ሁዳ ንጉሥ በዖ​ዝ​ያን ዘመን፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በዮ​አስ ልጅ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ዘመን፥ የም​ድር መና​ወጥ ከሆ​ነ​በት ከሁ​ለት ዓመት በፊት ስለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ያየው ቃል ይህ ነው።