የእግዚአብሔርን ቤተ መዛግብትና የንጉሡን ቤተ መዛግብት ሁሉ ወሰደ፤ ዳዊትም ከሱባ ንጉሥ ከአድርዓዛር ልጆች እጅ ወስዶ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጣቸውን የወርቅ ጦሮችና ሰሎሞን የሠራቸውን የወርቁን ጋሻና ጦር ሁሉ ወደ ግብፅ ወሰደ።
2 ነገሥት 14:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወርቁንና ብሩን ሁሉ፥ በእግዚአብሔርም ቤትና በንጉሥ ቤተ መዛግብት የነበሩትን ዕቃዎች ሁሉ፤ በመያዣም የተያዙትን ልጆች ወስዶ ወደ ሰማርያ ተመለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥቱ ግምጃ ቤቶች ያለውን ወርቅ ብርና ዕቃ በሙሉ፣ በዚያም የተገኘውን ዕቃ ሁሉ በመውሰድ ምርኮኞችንም ይዞ ወደ ሰማርያ ተመለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ያገኘውን ወርቅና ብር ሁሉ፥ የቤተ መቅደሱን ንዋያተ ቅድሳትና የቤተ መንግሥቱን ሀብት ሁሉ ጭኖ ወደ ሰማርያ ተመለሰ፤ በመያዣ ስም የተማረኩ ሰዎችንም ይዞ ሄደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም ያገኘውን ወርቅና ብር ሁሉ፥ የቤተ መቅደሱን ንዋያተ ቅድሳትና የቤተ መንግሥቱን ሀብት ሁሉ ጭኖ ወደ ሰማርያ ተመለሰ፤ በመያዣ ስም የተማረኩ ሰዎችንም ይዞ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወርቁንና ብሩን ሁሉ፥ በእግዚአብሔርም ቤትና በንጉሡ ቤት መዛግብት የነበሩትን ዕቃዎች ሁሉ፥ በመያዣም የተያዙትን ወስዶ ወደ ሰማርያ ተመለሰ። |
የእግዚአብሔርን ቤተ መዛግብትና የንጉሡን ቤተ መዛግብት ሁሉ ወሰደ፤ ዳዊትም ከሱባ ንጉሥ ከአድርዓዛር ልጆች እጅ ወስዶ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጣቸውን የወርቅ ጦሮችና ሰሎሞን የሠራቸውን የወርቁን ጋሻና ጦር ሁሉ ወደ ግብፅ ወሰደ።
አሳም በእግዚአብሔር ቤትና በንጉሥ ቤተ መዛግብት የተገኘውን ብርና ወርቅ ሁሉ ወስዶ ለአገልጋዮቹ ሰጣቸው፤ ንጉሡም አሳ በደማስቆ ለተቀመጠው ለአዚን ልጅ ለጤቤርማን ልጅ ለሶርያ ንጉሥ ለወልደ አዴር፥
እንዲሁም ንጉሡ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤት የአሠራው ሥራ ሁሉ ተፈጸመ። አባቱም ዳዊት የቀደሰውን፥ ራሱም የቀደሰውን፥ የብርና የወርቅ ዕቃ ሰሎሞን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በነበሩ ግምጃ ቤቶች አገባ።
የይሁዳም ንጉሥ ኢዮአስ አባቶቹ የይሁዳ ነገሥታት ኢዮሣፍጥና ኢዮራም፥ አካዝያስም የቀደሱትን ቅዱስ ነገር፥ እርሱም የቀደሰውን፥ በእግዚአብሔርም ቤትና በንጉሡም ቤተ መዛግብት የተገኘውን ወርቅ ሁሉ ወሰደ፤ ወደ ሶርያም ንጉሥ ወደ አዛሄል ላከው። እርሱም ከኢየሩሳሌም ተመለሰ።
አሁንም እንግዲህ ከጌታዬ ከአሦር ንጉሥ ጋር ተወራረድ፤ የሚቀመጡባቸውንም ሰዎች ማግኘት ቢቻልህ እኔ ሁለት ሺህ ፈረሶች እሰጥሃለሁ።
የእግዚአብሔርን ቤተ መዛግብት ሁሉ የንጉሡንም ቤተ መዛግብት ከዚያ አወጣ፤ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረው የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር መቅደስ የሠራውን የወርቁን ዕቃ ሁሉ ሰባበረ።