ደንገጡሮችሽም ሊቀበሉሽ ይወጣሉ፤ ልጅሽም ሞተ ይሉሻል፥ እስራኤልም ሁሉ ያለቅሱለታል፤ ይቀብሩትማል፤ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ዘንድ በኢዮርብዓም ቤት በዚህ ልጅ መልካም ነገር ተገኝቶበታልና ከኢዮርብዓም እርሱ ብቻ ይቀበራል።
2 ነገሥት 13:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮአካዝም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፥ በሰማርያም ቀበሩት፥ ልጁም ዮአስ በፋንታው ነገሠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮአካዝ ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ በሰማርያም ተቀበረ። ልጁ ዮአስም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮአካዝ ሞተ፤ በሰማርያም ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ዮአስ ነገሠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮአካዝ ሞተ፤ በሰማርያም ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ዮአስ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮአካዝም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በሰማርያም ቀበሩት፤ ልጁም ዮአስ በፋንታው ነገሠ። |
ደንገጡሮችሽም ሊቀበሉሽ ይወጣሉ፤ ልጅሽም ሞተ ይሉሻል፥ እስራኤልም ሁሉ ያለቅሱለታል፤ ይቀብሩትማል፤ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ዘንድ በኢዮርብዓም ቤት በዚህ ልጅ መልካም ነገር ተገኝቶበታልና ከኢዮርብዓም እርሱ ብቻ ይቀበራል።
በይሁዳ ንጉሥ በኢዮአስ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት የኢዮአካዝ ልጅ ዮአስ በእስራኤል ላይ በሰማርያ ዐሥራ ስድስት ዓመት ነገሠ።
ዮአስም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ ኢዮርብዓምም በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ፤ ዮአስም በሰማርያ ከእስራኤል ነገሥታት ጋር ተቀበረ።
የቀረውም የኢዮአካዝ ነገር፥ ያደረገውም ሁሉ፥ ኀይሉም፥ እነሆ፥ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?
በዚያን ጊዜም አሜስያስ፥ “ና እርስ በርሳችን ፊት ለፊት እንተያይ” ብሎ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዩ ልጅ ወደ ኢዮአካዝ ልጅ ወደ ዮአስ መልእክተኞችን ላከ።