እርሱም ያደረገው ይህ ነው በንጉሡ በሰሎሞን ላይ እጁን አነሣ፤ ሰሎሞንም በዳርቻ ያለ ቅጥርንና የአባቱን የዳዊትን ከተማ ቅጥር ሠርቶ ጨረሰ።
2 ነገሥት 12:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እያንዳንዱ ሰው ከሚያመጣው ካህናቱ ለራሳቸው ይውሰዱ፤ በመቅደስም ውስጥ የተናዱትን ይጠግኑበት” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እያንዳንዱም ካህን ገንዘቡን ከገንዘብ ያዡ እጅ ይቀበል፤ እንደ አስፈላጊነቱም በቤተ መቅደሱ ውስጥ የፈረሰውን ለማደስ ይዋል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እያንዳንዱ ካህን ከሚያገለግላቸው ሰዎች የሚገኘውን የገንዘብ መባ ሁሉ በጥንቃቄ የመጠበቅ ኃላፊነት ተሰጠው፤ ገንዘቡንም እንዳስፈላጊነቱ ለቤተ መቅደሱ ጥገና አገልግሎት እንዲያውሉት ነገራቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እያንዳንዱ ካህን ከሚያገለግላቸው ሰዎች የሚገኘውን የገንዘብ መባ ሁሉ በጥንቃቄ የመጠበቅ ኀላፊነት ተሰጠው፤ ገንዘቡንም እንዳስፈላጊነቱ ለቤተ መቅደሱ ጥገና አገልግሎት እንዲያውሉት ነገራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮአስም ካህናቱን “ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚገባውን የተቀደሰውን ገንዘብ ሁሉ፥ ስለ ነፍሱም ዋጋ የሚቀርበውን ገንዘብ፥ በልባቸውም ፈቃድ ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚያመጡትን ገንዘብ ሁሉ፥ |
እርሱም ያደረገው ይህ ነው በንጉሡ በሰሎሞን ላይ እጁን አነሣ፤ ሰሎሞንም በዳርቻ ያለ ቅጥርንና የአባቱን የዳዊትን ከተማ ቅጥር ሠርቶ ጨረሰ።
የተናደውን የእግዚአብሔርን ቤት ለመጠገን መክፈል ለሚያሻው ሁሉ ድንጋይንና እንጨትን ይገዙ ዘንድ፥ ለግንበኞችና ለድንጋይ ወቃሪዎች ይሰጡት ነበር።
ኢዮአስም ካህናቱን፥ “ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚገባውን የተቀደሰውን ገንዘብ ሁሉ፥ ስለ ነፍሱም ዋጋ የሚያቀርበውን ገንዘብ፥ በልባቸውም ፈቃድ ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚያመጡትን ገንዘብ ሁሉና፥
ነገር ግን እስከ ንጉሡ እስከ ኢዮአስ እስከ ሃያ ሦስተኛው ዓመት ድረስ ከመቅደሱ ውስጥ የተናዱትን ካህናቱ አልጠገኑትም ነበር።
“ወደ ታላቁ ካህን ወደ ኬልቅዩ ወጥተህ ደጃፉን የሚጠብቁ ከሕዝቡ የሰበሰቡትን ወደ እግዚአብሔር ቤት የገባውን ወርቅ ቍጠር።
የአባቶችም ቤቶች አለቆች፥ የእስራኤልም ልጆች አለቆች፥ ሻለቆችም፥ የመቶ አለቆችም፥ በእግዚአብሔር ቤት ሥራ የተሾሙና የንጉሡ ግንበኞች በፈቃዳቸው አቀረቡ።
ሕዝቡም ፈቅደው ሰጥተዋልና፥ በፍጹም ልባቸውም ለእግዚአብሔር በፈቃዳቸው አቅርበዋልና ደስ አላቸው፤ ንጉሡም ዳዊት ደግሞ ታላቅ ደስታ ደስ አለው።
ካህናትንና ሌዋውያንንም ሰብስቦ፥ “ወደ ይሁዳ ከተሞች ውጡ፤ የአምላካችሁንም ቤት በየዓመቱ ለማደስ የሚበቃ ከእስራኤል ሁሉ ገንዘብን ሰብስቡ፤ ነገሩንም ፈጥናችሁ አድርጉ” አላቸው። ሌዋውያን ግን አላፋጠኑም።
ጎቶልያ ከሐዲት ነበረችና ልጆችዋም የእግዚአብሔርን ቤት አፍርሰዋልና፤ በእግዚአብሔርም ቤት ተቀድሶ የነበረውን ሁሉ ለበኣሊም ሰጥተዋልና።
ይቈጠሩ ዘንድ የሚያልፉት ሁሉ የሚሰጡት ይህ ነው፤ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን የሰቅል ግማሽ ይሰጣል። ሰቅሉም ሃያ አቦሊ ነው፤ የሰቅሉም ግማሽ ለእግዚአብሔር ቍርባን ነው።
ከድሮ ዘመን የፈረሱት ስፍራዎችህ ይሠራሉ፤ መሠረትህም ለልጅ ልጅ ዘመን ይሆናል፤ አንተም፦ ሰባራውን ጠጋኝ፥ የመኖሪያ መንገድንም አዳሽ ትባላለህ።
“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ማናቸውም ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ለእግዚአብሔር ስእለት ቢሳል አንተ እንደምትገምተው መጠን ስለ ሰውነቱ ዋጋውን ይስጥ።
ከሰው እስከ እንስሳ ቢሆን፥ ለእግዚአብሔር ከሚያቀርቡት ሥጋ ሁሉ፥ መጀመሪያ የሚወለድ ሁሉ ለአንተ ይሆናል፤ ነገር ግን የሰውን በኵራት ፈጽሞ ትቤዠዋለህ፤ ያልነጹትንም እንስሳት በኵራት ትቤዣለህ።