የሰሎሞንንም የማዕዱን መብል፥ የብላቴኖቹንም አቀማመጥ፥ የሎሌዎቹንም ሥርዐት፥ አለባበሳቸውንም፥ ጠጅ አሳላፊዎቹንም፥ በእግዚአብሔርም ቤት የሚያቀርበውን መሥዋዕት ባየች ጊዜ ተደነቀች።
2 ነገሥት 11:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፥ “እንዲህ አድርጉ፤ በሰንበት ቀን ከምትገቡት ከእናንተ ከሦስት አንዱ እጅ በበር ተቀምጣችሁ የንጉሡን ቤት ዘብ ጠብቁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም ሲል አዘዛቸው፤ “እናንተ የምታደርጉት ይህ ነው፤ በሦስት ምድብ ሆናችሁ በሰንበት ዕለት ዘብ ከምትጠብቁት መካከል አንዱ እጅ ቤተ መንግሥቱን ይጠብቅ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚከተለውን ትእዛዝ ሰጣቸው፤ “በሰንበት ቀን ለዘብ ጥበቃ በምትሰማሩበት ጊዜ ከእናንተ ከሦስት አንዱ እጅ ቤተ መንግሥቱን ይጠብቅ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚከተለውን ትእዛዝ ሰጣቸው፤ “በሰንበት ቀን ለዘብ ጥበቃ በምትሰማሩበት ጊዜ ከእናንተ ከሦስት አንዱ እጅ ቤተ መንግሥቱን ይጠብቅ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ብሎ አዘዛቸው “እንዲህ አድርጉ፤ በሰንበት ቀን ከምትገቡት ከእናንተ ከሦስት አንዱ እጅ የንጉሡን ቤት ዘብ ጠብቁ፤ |
የሰሎሞንንም የማዕዱን መብል፥ የብላቴኖቹንም አቀማመጥ፥ የሎሌዎቹንም ሥርዐት፥ አለባበሳቸውንም፥ ጠጅ አሳላፊዎቹንም፥ በእግዚአብሔርም ቤት የሚያቀርበውን መሥዋዕት ባየች ጊዜ ተደነቀች።
መቶ አለቆቹንና ኮራውያንን፥ ዘበኞችንና የሀገሩንም ሕዝብ ሁሉ ወሰዳቸው፤ ንጉሡንም ከእግዚአብሔር ቤት አወጣው፤ በዘበኞችም በር መንገድ ወደ ንጉሡ ቤት አመጡት፤ በነገሥታቱም ዙፋን አስቀመጡት።
ሌላውም ከሦስት አንዱ እጅ በሰፊው መንገድ በበሩ በኩል ተቀመጡ፤ ሦስተኛውም እጅ ከዘበኞች ቤት በኋላ ባለው በር ሁኑ፤ ቤቱንም አጽንታችሁ ጠብቁ፤
በእግዚአብሔርም ቤት የዙፋኑን መሠረት ሠራ፤ ስለ አሦርም ንጉሥ በውጭ ያለውን የንጉሡን መግቢያ ወደ እግዚአብሔር ቤት አዞረው።
ለእግዚአብሔርም ቤት አገልግሎት የምስክሩን ድንኳን ሥርዐት፥ የወንድሞቻቸውን የአሮንን ልጆች ሥርዐት ለመጠበቅ ሹሞአቸው ነበር።
የይሁዳም አለቆች ይህን በሰሙ ጊዜ ከንጉሡ ቤት ወደ እግዚአብሔር ቤት ወጡ፤ በአዲሱም በእግዚአብሔር ቤት ደጅ መግቢያ ተቀመጡ።