ዳዊትም ለሱባን ንጉሥ ለአድርአዛር አገልጋዮች የነበሩትን ጋሻ አግሬዎች ወሰደ፤ ወደ ኢየሩሳሌምም አመጣቸው። እነዚህንም የግብፅ ንጉሥ ሱስቀም በሰሎሞን ልጅ በሮብዓም ዘመን ወደ ኢየሩሳሌም በወጣ ጊዜ ወሰዳቸው።
2 ነገሥት 11:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮዳሄም በእግዚአብሔር ቤት የነበረውን የንጉሡን የዳዊትን ሰይፍና ጦር ሁሉ ለመቶ አለቆች ሰጣቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህኑም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የነበሩትን የንጉሥ ዳዊትን ጦሮችና ጋሻዎች ለመቶ አለቆቹ ሰጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮዳሄም በቤተ መቅደስ ተቀምጠው ይጠበቁ የነበሩትን የንጉሥ ዳዊትን ጦሮችና ጋሻዎች አውጥቶ ለጦር አለቆቹ ሰጣቸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮዳሄም በቤተ መቅደስ ተቀምጠው ይጠበቁ የነበሩትን የንጉሥ ዳዊትን ጦሮችና ጋሻዎች አውጥቶ ለጦር አለቆቹ ሰጣቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም በእግዚአብሔር ቤት የነበረውን የንጉሡን የዳዊትን ጋሻና ጦር ሁሉ ለመቶ አለቆች ሰጣቸው። |
ዳዊትም ለሱባን ንጉሥ ለአድርአዛር አገልጋዮች የነበሩትን ጋሻ አግሬዎች ወሰደ፤ ወደ ኢየሩሳሌምም አመጣቸው። እነዚህንም የግብፅ ንጉሥ ሱስቀም በሰሎሞን ልጅ በሮብዓም ዘመን ወደ ኢየሩሳሌም በወጣ ጊዜ ወሰዳቸው።
ዘበኞቹም ሁሉ እያንዳንዳቸው የጦር ዕቃቸውን በእጃቸው ይዘው በንጉሡ ዙሪያ ከቤቱ ቀኝ እስከ ቤቱ ግራ ድረስ በመሠዊያውና በቤቱ አጠገብ ቆሙ።
ሰሎሞንም አባቱ ዳዊት የቀደሰውን ብሩንና ወርቁን፥ የመገልገያ ዕቃውንም ሁሉ አምጥቶ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በነበረው ግምጃ ቤት አገባ።
ካህኑም፥ “በኤላ ሸለቆ የገደልኸው የፍልስጥኤማዊው የጎልያድ ሰይፍ እነሆ፥ በመጐናጸፊያ ተጠቅልላ አለች፤ የምትወስዳት ከሆነ ውሰዳት፤ ከእርስዋ በቀር ሌላ ከዚህ የለምና” አለው። ዳዊትም፥ “ከእርስዋ በቀር ሌላ ከሌለ እርስዋን ስጠኝ” አለው። እርሱም ሰጠው።