Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 5:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ሰሎ​ሞ​ንም አባቱ ዳዊት የቀ​ደ​ሰ​ውን ብሩ​ንና ወር​ቁን፥ የመ​ገ​ል​ገያ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ አም​ጥቶ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ በነ​በ​ረው ግምጃ ቤት አገባ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሠራው ሥራ ሁሉ ከተጠናቀቀ በኋላ፣ አባቱ ዳዊት የቀደሰውን ብሩንና ወርቁን፣ ዕቃዎቹንም ሁሉ አምጥቶ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ግምጃ ቤት አኖራቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 እንዲሁም ሰሎሞን ለጌታ ቤት የሚሠራውን ሥራ ሁሉ ጨረሰ። አባቱም ዳዊት የቀደሰውን የብርና የወርቅ ዕቃ ሁሉ ሰሎሞን አምጥቶ በጌታ ቤት ውስጥ በነበረው ግምጃ ቤት አኖረው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ንጉሥ ሰሎሞን የቤተ መቅደሱን ሥራ ሁሉ ከፈጸመ በኋላ አባቱ ዳዊት ለእግዚአብሔር የተለዩ ያደረጋቸውን ብርና ወርቅ እንዲሁም ሌሎችን ዕቃዎች ሁሉ በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሚገኘው የዕቃ ግምጃ ቤት አኖራቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እንዲሁም ሰሎሞን ስለ እግዚአብሔር ቤት የሠራው ሥራ ሁሉ ተጨረሰ። አባቱም ዳዊት የቀደሰውን የብርና የወርቅ ዕቃ ሁሉ ሰሎሞን አምጥቶ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በነበረው ግምጃ ቤት አኖረው።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 5:1
7 Referencias Cruzadas  

እን​ዲ​ሁም ንጉሡ ሰሎ​ሞን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የአ​ሠ​ራው ሥራ ሁሉ ተፈ​ጸመ። አባ​ቱም ዳዊት የቀ​ደ​ሰ​ውን፥ ራሱም የቀ​ደ​ሰ​ውን፥ የብ​ርና የወ​ርቅ ዕቃ ሰሎ​ሞን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ በነ​በሩ ግምጃ ቤቶች አገባ።


አሁ​ንም፥ እነሆ፥ በድ​ህ​ነቴ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት መቶ ሺህ መክ​ሊት ወር​ቅና አንድ ሚሊ​ዮን መክ​ሊት ብር፥ ሚዛ​ንም የሌ​ላ​ቸው ብዙ ናስና ብረት አዘ​ጋ​ጅ​ቻ​ለሁ፤ ደግ​ሞም የማ​ይ​ቈ​ጠር ብዙ የዝ​ግባ እን​ጨ​ትና ድን​ጋ​ዮች አዘ​ጋ​ጅ​ቻ​ለሁ፤ አን​ተም ልጄ ከዚያ በላይ ጨምር።


እር​ሱ​ንም ንጉሥ ዳዊት ከሀ​ገ​ሮች ሁሉ አም​ጥቶ ከቀ​ደ​ሰው ከወ​ር​ቁና ከብሩ ጋር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀደሰ፤


ንጉ​ሡም ዳዊት ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ከኤ​ዶ​ምና ከሞ​ዓብ፥ ከአ​ሞ​ንም ልጆች፥ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም፥ ከአ​ማ​ሌ​ቅም ከማ​ረ​ከው ብርና ወርቅ ጋር እነ​ዚ​ህን ደግሞ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀደሰ።


ውስ​ጠ​ኛው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ደጅና ወደ ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ መግ​ቢያ የሚ​ወ​ስ​ደው የው​ስ​ጠ​ኛ​ውም የቤተ መቅ​ደሱ ደጆች የወ​ርቅ ነበሩ። እን​ዲ​ሁም ሰሎ​ሞን ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሠ​ራው ሥራ ሁሉ ተፈ​ጸመ።


አም​ስ​ቱ​ንም መቀ​መ​ጫ​ዎች በቤቱ ቀኝ፥ አም​ስ​ቱ​ንም በቤቱ ግራ አኖ​ራ​ቸው፤ ኩሬ​ው​ንም በቤቱ ቀኝ በአ​ዜብ ፊት ለፊት በስ​ተ​ም​ሥ​ራቅ አኖ​ረው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios