2 ነገሥት 10:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዩ ከይሁዳ ንጉሥ ከአካዝያስ ወንድሞች ጋር ተገናኝቶ፥ “እናንተ እነማን ናችሁ?” አለ፤ እነርሱም፥ “እኛ የይሁዳ ንጉሥ የአካዝያስ ወንድሞች ነን፤ የንጉሡንና የእቴጌዪቱን ልጆች ደኅንነት እንነግረው ዘንድ ወረድን” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዩ ከይሁዳ ንጉሥ ከአካዝያስ ሥጋ ዘመዶች ጥቂቶቹን አግኝቶ፣ “እናንተ እነማን ናችሁ?” ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም፣ “እኛ የአካዝያስ ሥጋ ዘመዶች ነን፤ ንጉሣዊውን ቤተ ሰብና የእቴጌዪቱን ልጆች ለመጠየቅ ወደዚህ ወርደን መጥተናል” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሟቹ የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስ ዘመዶች መካከል ጥቂቶቹን አግኝቶ “እናንተ እነማን ናችሁ?” ሲል ጠየቀ። እነርሱም “እኛ የአካዝያስ ዘመዶች ነን፤ አሁንም የንግሥት ኤልዛቤልን ልጆችና የቀሩትንም ንጉሣውያን ቤተሰብ እጅ ለመንሣት ወደ ኢይዝራኤል መሄዳችን ነው” ሲሉ መለሱለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሟቹ የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስ ዘመዶች መካከል ጥቂቶቹን አግኝቶ “እናንተ እነማን ናችሁ?” ሲል ጠየቀ። እነርሱም “እኛ የአካዝያስ ዘመዶች ነን፤ አሁንም የንግሥት ኤልዛቤልን ልጆችና የቀሩትንም ንጉሣውያን ቤተሰብ እጅ ለመንሣት ወደ ኢይዝራኤል መሄዳችን ነው” ሲሉ መለሱለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዩ ከይሁዳ ንጉሥ ከአካዝያስ ወንድሞች ጋር ተገናኝቶ “እናንተ እነማን ናችሁ?” አለ። እነርሱም “እኛ የአካዝያስ ወንድሞች ነን፤ የንጉሡንና የእቴጌይቱን ልጆች ደኅንነት ለመጠየቅ እንወርዳለን፤” አሉት። |
እርሱም፥ “በሕይወታቸው ያዙአቸው” ብሎ አዘዘ። በበግ ጠባቂዎች ቤትም አጠገብ አርባ ሁለቱን ሰዎች ገደሉአቸው፤ ከእነርሱም አንድ ሰው እንኳ አላስቀረም።
ኢዮራምም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፥ በአባቱም በዳዊት ከተማ ከአባቶቹ ጋር ተቀበረ፤ በፋንታውም ልጁ አካዝያስ ነገሠ።
ንጉሡም ኢዮራም ከሶርያ ንጉሥ ከአዛሄል ጋር በተዋጋ ጊዜ ሶርያውያን በሬማት ያቈሰሉትን ቍስል ይታከም ዘንድ ወደ ኢይዝራኤል ተመለሰ። የአክዓብም ልጅ ኢዮራም ታምሞ ነበርና የኢዮራም ልጅ አካዝያስ ሊያየው ወደ ኢይዝራኤል ወረደ።
ወደ ይሁዳም ወጡ፤ በረቱባቸውም፤ የንጉሡንም ቤት ዕቃ ሁሉ፥ ወንዶች ልጆቹንም፥ ሴቶች ልጆቹንም ወሰዱ፤ ከታናሹም ልጅ ከአካዝያስ በቀር ልጅ አልቀረለትም።
ጢማቸውን ላጭተው፥ ልብሳቸውንም ቀድደው እያለቀሱ ወደ እግዚአብሔር ቤት ያቀርቡ ዘንድ የእህል ቍርባንና ዕጣን በእጃቸው የያዙ፥ ሰማንያ ሰዎች ከሴኬምና ከሴሎ፥ ከሰማርያም መጡ።