ከዚህም ነገር በኋላ የእግዚአብሔር ቃል በራእይ ወደ አብራም መጣ፤ እንዲህ ሲል፥ “አብራም ሆይ፥ አትፍራ፤ እኔ ጋሻ እሆንሃለሁ፤ ዋጋህም በእኔ ዘንድ እጅግ ብዙ ነው።”
2 ነገሥት 1:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም መልአክ ኤልያስን፥ “ከእርሱ ጋር ውረድ፤ ከፊታቸውም የተነሣ አትፍራ” ብሎ ነገረው። ኤልያስም ተነሥቶ ከእርሱ ጋር ወደ ንጉሡ ወረደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔርም መልአክ ኤልያስን፣ “ዐብረኸው ውረድ፤ ደግሞም አትፍራው” አለው። ስለዚህ ኤልያስ ተነሣ፤ ዐብሮትም ወደ ንጉሡ ወረደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህም ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ኤልያስን “ከእርሱ ጋር አብረህ ውረድ፤ ከቶም አትፍራ” አለው። ስለዚህም ኤልያስ ከመኰንኑ ጋር ወደ ንጉሡ ወረደ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህም ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ኤልያስን “ከእርሱ ጋር አብረህ ውረድ፤ ከቶም አትፍራ” አለው። ስለዚህም ኤልያስ ከመኰንኑ ጋር ወደ ንጉሡ ወረደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርም መልአክ ኤልያስን “ከእርሱ ጋር ውረድ፤ አትፍራውም፤” አለው። ተነሥቶም ከእርሱ ጋር ወደ ንጉሡ ወረደ። |
ከዚህም ነገር በኋላ የእግዚአብሔር ቃል በራእይ ወደ አብራም መጣ፤ እንዲህ ሲል፥ “አብራም ሆይ፥ አትፍራ፤ እኔ ጋሻ እሆንሃለሁ፤ ዋጋህም በእኔ ዘንድ እጅግ ብዙ ነው።”
እነሆ፥ እሳት ከሰማይ ወርዳ የፊተኞቹን ሁለቱን የአምሳ አለቆችና አምሳ አምሳውን ሰዎቻቸውን በላች፤ አሁን ግን ነፍሴ በፊትህ የከበረች ትሁን።”
የእግዚአብሔርም መልአክ ቴስብያዊውን ኤልያስን ጠርቶ፥ “ተነሣ፤ የሰማርያን ንጉሥ መልእክተኞች ለመገናኘት ሂድና፦ የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ትጠይቁ ዘንድ የምትሄዱት በእስራኤል ዘንድ አምላክ ስለሌለ ነውን?
አቤቱ፥ አምላኬ ሆይ፥ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ ቸልም አትበለኝ። ቸል ብትለኝ ግን ወደ ጕድጓድ እንደሚወርዱት እሆናለሁ።
እኔ ነኝ፤ የማጽናናሽ እኔ ነኝ፤ አንቺ እንግዲህ ዕወቂ፤ ማንን ፈራሽ? የሚሞተውን ሰው እንደ ሣርም የሚጠወልገውን የሰው ልጅ ነውን?
አንተ ግን ወገብህን ታጠቅ፤ ተነሥም፤ ያዘዝሁህንም ሁሉ ንገራቸው፤ ከፊታቸውም የተነሣ አትፍራ። በፊታቸውም አትደንግጥ አድንህ ዘንድ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና ይላል እግዚአብሔር።
አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ኩርንችትና እሾህ ከአንተ ጋር ቢኖሩም፥ አንተም በጊንጦች መካከል ብትቀመጥ፥ አትፍራቸው፤ ቃላቸውንም አትፍራ፤ አንተ ቃላቸውን አትፍራ፤ ከፊታቸውም የተነሣ አትደንግጥ፤ እነርሱ ዐመፀኛ ቤት ናቸውና።