La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ቆሮንቶስ 8:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ፈቃድ ካለም፥ ሰው በሚ​ቻ​ለው መጠን ቢሰጥ ይመ​ሰ​ገ​ናል፤ በማ​ይ​ቻ​ለ​ውም መጠን አይ​ደ​ለም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ለመስጠት በጎ ፈቃድ ካለን ስጦታው ተቀባይነት የሚያገኘው ባለን መጠን ስንሰጥ እንጂ፣ በሌለን መጠን ለመስጠት ስንሞክር አይደለም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በጎ ፈቃድ ቢኖር፥ ባለው ባለው መጠን ተቀባይነት ይኖረዋል እንጂ የሌላውን አይጠበቅበትም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ለመስጠት መልካም ፈቃድ ካለ የሰው ልግሥና ተቀባይነት የሚያገኘው ባለው መጠን ሲሰጥ እንጂ በሌለው መጠን ሲሰጥ አይደለም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በጎ ፈቃድ ቢኖር፥ እንዳለው መጠን የተወደደ ይሆናል እንጂ እንደሌለው መጠን አይደለም።

Ver Capítulo



2 ቆሮንቶስ 8:12
21 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አባ​ቴን ዳዊ​ትን፦ ለስሜ ቤት ትሠራ ዘንድ በል​ብህ አስ​በ​ሃ​ልና ይህን በል​ብህ ማሰ​ብህ መል​ካም አደ​ረ​ግህ።


“የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በል​ባ​ችሁ ያሰ​ባ​ች​ሁ​ትን ከገ​ን​ዘ​ባ​ችሁ መባ አም​ጡ​ልኝ” በላ​ቸው።


ስዕ​ለት የተ​ሳለ ሁሉ፥ የብ​ር​ንም፥ የና​ስ​ንም ስጦታ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍር​ባን አቀ​ረበ፤ የማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት ያለው ሁሉ ለድ​ን​ኳኑ ማገ​ል​ገያ ለሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ገው ሥራ አመጣ።


ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም ያመጡ ዘንድ ልባ​ቸው ያስ​ነ​ሣ​ቸው ወን​ዶ​ችና ሴቶች ሁሉ ሙሴ ይሠራ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላዘ​ዘው ሥራ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስጦታ በፈ​ቃ​ዳ​ቸው አመጡ።


ከእ​ና​ንተ ዘንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍር​ባ​ንን አቅ​ርቡ፤ የልብ ፈቃድ ያለው ከገ​ን​ዘቡ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያምጣ፤ ወር​ቅና ብር፥ ናስም፤


ምጽዋት ለሰው ፍሬ ነው፤ ከሐሰተኛ ባለጠጋም እውነተኛ ድሃ ይሻላል።


እንዲሁም ሁለት የተቀበለው ሌላ ሁለት አተረፈ።


ሁለት መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ ‘ጌታ ሆይ! ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ ሁለት መክሊት አተረፍሁበት፤’ አለ።


“በጥ​ቂት የሚ​ታ​መን በብዙ ይታ​መ​ናል፤ በጥ​ቂት የሚ​ያ​ም​ፅም በብ​ዙም ቢሆን ያም​ፃል።


አሁ​ንም አድ​ርጉ፤ ፈጽ​ሙም፤ መፍ​ቀድ ከመ​ሻት ነውና፤ ማድ​ረ​ግም ከማ​ግ​ኘት ነውና።


በዚህ ወራት ተካ​ክ​ላ​ችሁ እን​ድ​ት​ኖሩ ነው እንጂ ሌላው እን​ዲ​ያ​ርፍ እና​ን​ተን የም​ና​ስ​ጨ​ንቅ አይ​ደ​ለም።


ይህም ብቻ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብ​ርና የእ​ኛን በጎ ፈቃድ ለማ​ሳ​የት በም​ና​ገ​ለ​ግ​ል​ባት በዚች ጸጋ ከእኛ ጋር አንድ ይሆን ዘንድ በአ​ብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ተሾመ።


ሁሉ ልቡ እንደ ወደደ ያድ​ርግ፤ በደ​ስታ ይስጡ እንጂ በግድ አይ​ሆ​ንም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በደ​ስታ የሚ​ሰ​ጠ​ውን ይወ​ዳ​ልና።


ልዩ ልዩን የእግዚአብሔርን ጸጋ ደጋግ መጋቢዎች እንደ መሆናችሁ፥ እያንዳንዳችሁ የጸጋን ስጦታ እንደ ተቀበላችሁ መጠን በዚያው ጸጋ እርስ በርሳችሁ አገልግሉ፤