2 ቆሮንቶስ 5:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከለበስነውም በኋላ ዕራቍታችንን የምንገኝ አይደለንም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በርግጥ ከለበስነው ዕራቍታችንን ሆነን አንገኝም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለብሰን ራቁታችንን አንገኝም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱንም ስንለብስ ራቁታችንን ሆነን አንገኝም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሰማይም የሚሆነውን መኖሪያችንን እንድንለብስ እንናፍቃለንና ለብሰን ራቁታችንን አንገኝም። |
በዚህ ቤት ውስጥ ሳለንም ከከባድነቱ የተነሣ እጅግ እናዝናለን፤ ነገር ግን ሟች በሕይወት ይዋጥ ዘንድ ሌላ ልንለብስ እንጂ ልንገፈፍ አንወድም።
ባለ ጠጋ እንድትሆን በእሳት የነጠረውን ወርቅ፥ ተጐናጽፈህም የራቁትነትህ ኃፍረት እንዳይገለጥ ነጭ ልብስን፥ እንድታይም ዐይኖችህን የምትኳለውን ኵል ከእኔ ትገዛ ዘንድ እመክርሃለሁ።