2 ቆሮንቶስ 3:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስከ ዛሬም የሙሴን ሕግ ሲያነብቡ ያ መጋረጃ ልባቸውን ይሸፍናቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስከ ዛሬም ድረስ የሙሴ መጻሕፍት በተነበቡ ቍጥር መሸፈኛው ልቡናቸውን ይሸፍናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ የሙሴ መጻሕፍት በተነበቡ ቍጥር ያ መጋረጃ በልባቸው ይኖራል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዛሬም እንኳ ቢሆን የሕግ መጻሕፍትን ባነበቡ ቊጥር ልቡናቸው በመሸፈኛው ይሸፈናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ የሙሴ መጻሕፍት በተነበቡ ጊዜ ሁሉ ያ መጋረጃ በልባቸው ይኖራል፤ |
ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ ልባቸው ተሸፍኖአል፤ ያም መጋረጃ ብሉይ ኪዳን በተነበበት ዘመን ሁሉ ጸንቶ ኖሮአል፤ ክርስቶስ እስኪያሳልፈው ድረስ አልተገለጠምና።