ከጥቂት ቀን በኋላም ጳውሎስ በርናባስን፦“እንግዲህስ እንመለስና የእግዚአብሔርን ቃል ባስተማርንባቸው ሀገሮች ያሉትን ወንድሞች እንጐብኛቸው፤ እንዴት እንዳሉም እንወቅ” አለው።
2 ቆሮንቶስ 11:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቀረውንም ነገር ሳልቈጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሌላውን ነገር ሳልቈጥር፣ ዕለት ዕለት የሚያስጨንቀኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ሐሳብ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሌላው ሳይቆጠር፥ በየዕለቱ የሚከብድብኝ ለአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ መጨነቄ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌላውንም ሁሉ ነገር ሳልቈጥር ስለ አብያተ ክርስቲያን ሁሉ በየቀኑ በማሰብ እጨነቅ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቀረውንም ነገር ሳልቆጥር፥ ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው። |
ከጥቂት ቀን በኋላም ጳውሎስ በርናባስን፦“እንግዲህስ እንመለስና የእግዚአብሔርን ቃል ባስተማርንባቸው ሀገሮች ያሉትን ወንድሞች እንጐብኛቸው፤ እንዴት እንዳሉም እንወቅ” አለው።
በይሁዳ፥ በሰማርያና በገሊላ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ በሰላም ኖሩ፤ ታነጹም፤ እግዚአብሔርንም በመፍራት ጸንተው ኖሩ፤ ሕዝቡም በመንፈስ ቅዱስ አጽናኝነት በዙ።
በአሕዛብ መካከል ኢየሱስ ክርስቶስን አገለግል ዘንድ፥ ለእግዚአብሔር ወንጌልም እገዛ ዘንድ፥ በእኔ ትምህርት አሕዛብ በመንፈስ ቅዱስ የተወደደና የተመረጠ መሥዋዕት ይሆኑ ዘንድ።
ስለ እኔ ሰውነታቸውን ለመከራ አሳልፈው ሰጥተዋልና፤ የማመሰግናቸውም እኔ ብቻ አይደለሁም፤ ከአሕዛብ ያመኑ ምእመናን ሁሉ ያመሰግኑአቸዋል እንጂ።
ነገር ግን ሁሉ እግዚአብሔር እንደ አደለው፥ ሁሉም እግዚአብሔር እንደ ጠራው እንዲሁ ይኑር፤ ለአብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ እንዲህ ሥርዐት እንሠራለን።
ስለ እናንተ እና በሎዶቅያ ስላሉ፥ ፊቴንም በሥጋ ስላላዩት ምእመናን ሁሉ ምን ያህል እንደምጋደል ልታውቁ እወዳለሁ።