Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ቆሮንቶስ 11:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ሌላውንም ሁሉ ነገር ሳልቈጥር ስለ አብያተ ክርስቲያን ሁሉ በየቀኑ በማሰብ እጨነቅ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ሌላውን ነገር ሳልቈጥር፣ ዕለት ዕለት የሚያስጨንቀኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ሐሳብ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ሌላው ሳይቆጠር፥ በየዕለቱ የሚከብድብኝ ለአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ መጨነቄ ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 የቀ​ረ​ው​ንም ነገር ሳል​ቈ​ጥር ዕለት ዕለት የሚ​ከ​ብ​ድ​ብኝ የአ​ብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ሁሉ አሳብ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 የቀረውንም ነገር ሳልቆጥር፥ ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው።

Ver Capítulo Copiar




2 ቆሮንቶስ 11:28
12 Referencias Cruzadas  

እያንዳንዱ ጌታ በሰጠው ስጦታና እግዚአብሔር በጠራው ጊዜ በነበረበት ሁኔታ ይኑር፤ ለአብያተ ክርስቲያን ሁሉ የሰጠሁት መመሪያ ይህንኑ ነው።


ይህም ጸጋ የተሰጠኝ የእግዚአብሔርን የምሥራች ቃል ለአሕዛብ በማብሠር እንደ ካህን ሆኜ ኢየሱስ ክርስቶስን ለማገልገል ነው፤ ስለዚህ አሕዛብ በመንፈስ ቅዱስ የተቀደሰና እግዚአብሔርንም ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ አገለግላለሁ።


ስለ እናንተና በሎዶቅያ ስላሉት ሰዎች እንዲሁም ፊቴን እንኳ አይተውት ስለማያውቁ ሰዎች ሁሉ ምን ያኽል ብርቱ ትግል እንደማደርግ ልታውቁ እወዳለሁ።


እነርሱ በእኔ ምትክ ለመሞት እንኳ የተዘጋጁ ነበሩ፤ በዚህም ዘወትር አመሰግናቸዋለሁ፤ እኔም ብቻ ሳልሆን ከአሕዛብነት ወደ ክርስትና የተመለሱ ምእመናን አብያተ ክርስቲያን ጭምር ያመሰግኑአቸዋል።


አሁን እንግዲህ የምናገረው ለእናንተ ለአሕዛብ ነው፤ የአሕዛብም ሐዋርያ እንደ መሆኔ መጠን በአገልግሎቴ ክብር ይሰማኛል፤


እዚያም ጥቂት ጊዜ ቈየ፤ ከዚህ በኋላ በገላትያና በፍርግያ ምድር ከቦታ ወደ ቦታ እየተዘዋወረ አማኞችን አበረታታ።


የሠለጠኑትንም ሆነ ያልሠለጠኑትን፥ የተማሩትንም ሆነ ያልተማሩትን ሕዝቦች የማስተማር ግዴታ አለብኝ።


በእነዚያ በሚያልፍባቸው ስፍራዎች ምእመናንን በብዙ ምክር እያበረታታ ወደ ግሪክ አገር ሄደ።


ከጥቂት ቀኖች በኋላ ጳውሎስ በርናባስን “ና እንመለስና ከዚህ በፊት የጌታን ቃል ባበሠርንባቸው ከተሞች ሁሉ ያሉትን ወንድሞች እንጐብኝ፤ እንዴት እንደ ሆኑም እንወቅ” አለው።


በይሁዳ፥ በገሊላና በሰማርያ ሁሉ ያለችው ቤተ ክርስቲያን ሰላም አገኘች፤ በረታችም፤ ጌታን እያከበረችና በመንፈስ ቅዱስ እየተጽናናች በቊጥር አደገች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios