በቤቱ ውስጥ ላለው ወለል ሁለቱን የናስ አዕማድ ሠራ፤ የአንዱም ዓምድ ቁመት ዐሥራ ስምንት ክንድ ነበረ፤ የዙሪያውም መጠን ዐሥራ ሁለት ክንድ ነበረ፤ የዓምዱም ውፍረት አንድ ጋት ነበረ፤ ውስጠ ክፍትም ነበረ። ሁለተኛውም ዓምድ እንዲሁ ነበረ።
2 ዜና መዋዕል 4:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁለት ዐምዶችንና በሁለቱ ዐምዶች ላይ ጕልላቶችን፥ በዐምዶቹም ራሶች ላይ ያሉትን ጕልላቶች የሚሸፍኑ ሁለት መርበቦችን ሠራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁለቱን አዕማድ፣ በአዕማዱ ጫፎች ላይ ያሉትን ሁለት ባለሳሕን ጕልላቶችን፤ በአዕማዱ ላይ ያሉትን ባለሳሕን ቅርጽ ሁለት ጕልላቶችን ያስጌጡትን ሁለት መረቦች፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁለቱን ዓምዶች፥ ጽዋዎቹንም፥ በዓምዶቹም ላይ የነበሩትን ሁለት ጉልላቶች፥ በዓምዶቹም ላይ የነበሩትን የጉልላቶች ሁለቱን ጽዋዎች የሚሸፍኑትን ሁለቱን መርበቦች ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለቱን አዕማድ፥ ጽዋዎቹንም፥ በፃምዶቹምም ላይ የነበሩትን ሁለት ጕልላቶች፥ በዓምዶቹም ላይ የነበሩትን የጕልላቶች ሁለቱን ጽዋዎች የሚሸፍኑትን ሁለቱን መርበቦች ሠራ። |
በቤቱ ውስጥ ላለው ወለል ሁለቱን የናስ አዕማድ ሠራ፤ የአንዱም ዓምድ ቁመት ዐሥራ ስምንት ክንድ ነበረ፤ የዙሪያውም መጠን ዐሥራ ሁለት ክንድ ነበረ፤ የዓምዱም ውፍረት አንድ ጋት ነበረ፤ ውስጠ ክፍትም ነበረ። ሁለተኛውም ዓምድ እንዲሁ ነበረ።
ሁለቱንም አዕማድ፥ በሁለቱም አዕማድ ራስ ላይ የነበሩትን ኩብ የሚመስሉትን ጕልላቶች፥ በሁለቱም አዕማድ ላይ የነበሩትን ሁለቱን ጕልላቶች የሚሸፍኑትን ሁለቱን መርበቦች፥
ኪራምም ምንቸቶቹንና መጫሪያዎቹን፥ በመሠዊያው ቤት ያሉ ማንኪያዎችንና የመገልገያውን ዕቃ ሁሉ ሠራ። ኪራምም ለንጉሡ ለሰሎሞን በእግዚአብሔር ቤት የሠራውን ሥራ ሁሉ ጨረሰ።
በሁለቱም መርበቦች አራት መቶ የወርቅ ሻኵራዎችንና በዐምዶቹ ላይ ያሉትን ሁለት ጕልላቶች በሁለት ጎኖች የሚሸፍኑትን ሮማኖች ሠራ።