ነገር ግን በኮረብቶቹ ላይ ያሉትን መስገጃዎች አላስወገደም፤ ሕዝቡም ገና በኮረብቶቹ ላይ ባሉት መስገጃዎች ይሠዋና ያጥን ነበር።
2 ዜና መዋዕል 25:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔርም ፊት ቅን ነገርን አደረገ፤ ነገር ግን በፍጹም ልብ አይደለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም በእግዚአብሔር ፊት መልካም ነገር አደረገ፤ ነገር ግን በፍጹም ልቡ አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍጹምም ልብ ሳይኖረው አሜስያስ በጌታ ፊት ቅን ነገር አደረገ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሜስያስ አብዛኛውን ጊዜ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነገር ያደርግ ነበር፤ ይሁን እንጂ አንዳንድ ጊዜ የሚያደርገውን ነገር በሙሉ ልብ አያደርግም ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእግዚአብሔርም ፊት ቅን ነገር አደረገ፤ ነገር ግን በፍጹም ልብ አይደለም። |
ነገር ግን በኮረብቶቹ ላይ ያሉትን መስገጃዎች አላስወገደም፤ ሕዝቡም ገና በኮረብቶቹ ላይ ባሉት መስገጃዎች ይሠዋና ያጥን ነበር።
አሜስያስም የኤዶምያስን ሰዎች ከገደለ በኋላ የሴይርን ልጆች አማልክት አመጣ፤ የእርሱም አማልክት ይሆኑ ዘንድ አቆማቸው፤ በፊታቸውም ይሰግድላቸውና ይሠዋላቸው ነበር።
ጌታም አለ፥ “ይህ ሕዝብ በከንፈሮቹ ያከብረኛልና፥ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነውና፥ በከንቱ ያመልኩኛል፤ ሰው ሠራሽ ትምህርትም ያስተምራሉ፤
እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን፥ “ፊቱን፥ የቁመቱንም ዘለግታ አትይ፤ ሰው እንደሚያይ እግዚአብሔር አያይምና ናቅሁት፤ ሰው ፊትን ያያል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል” አለው።