Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 25:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 አሜስያስ አብዛኛውን ጊዜ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነገር ያደርግ ነበር፤ ይሁን እንጂ አንዳንድ ጊዜ የሚያደርገውን ነገር በሙሉ ልብ አያደርግም ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እርሱም በእግዚአብሔር ፊት መልካም ነገር አደረገ፤ ነገር ግን በፍጹም ልቡ አልነበረም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ፍጹምም ልብ ሳይኖረው አሜስያስ በጌታ ፊት ቅን ነገር አደረገ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቅን ነገ​ርን አደ​ረገ፤ ነገር ግን በፍ​ጹም ልብ አይ​ደ​ለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 በእግዚአብሔርም ፊት ቅን ነገር አደረገ፤ ነገር ግን በፍጹም ልብ አይደለም።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 25:2
12 Referencias Cruzadas  

ይኸውም በየኰረብታዎች ላይ የተሠሩትን የአሕዛብ ማምለኪያዎችን አላፈረሰም፤ ከዚህም የተነሣ ሕዝቡ በየኮረብታዎቹ መሥዋዕት ማቅረቡንና ዕጣን ማጠኑን እንደ ቀጠለ ነበር።


ካህኑ ዮዳሄ በሕይወት በነበረበት ዘመን ሁሉ ኢዮአስ፥ እግዚአብሔርን ደስ የሚያስኝ ነገር ያደርግ ነበር፤


አሜስያስ ኤዶማውያንን ድል አድርጎ በተመለሰ ጊዜ ጣዖቶቻቸውን ይዞ መጣ፤ አማልክት አድርጎም በማቆም ሰገደላቸው፤ ዕጣንም አጠነላቸው፤


መንግሥቱን እንዳጠናከረ ወዲያውኑ አባቱን የገደሉትን ባለሥልጣኖች በሙሉ በሞት ቀጣ፤


ዖዝያ የአባቱን መልካም አርአያነት በመከተል እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነገር አደረገ፤


ለእርሱ ታማኞች አልነበሩም፤ የእርሱንም ቃል ኪዳን አላከበሩም።


ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ይህ ሕዝብ በአፉ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤ እኔንም የሚያመልከኝ ሰው ሠራሽ ወግና ሥርዓትን እያስተማረ በከንቱ ነው።


ልባቸው በተንኰል የተሞላ ነው፤ የበደላቸውንም ዋጋ ያገኛሉ፤ እግዚአብሔር መሠዊያዎቻቸውን ሁሉ ይሰባብራል፤ የጣዖት መስገጃ ዐምዶቻቸውንም ያፈራርሳል።


ልብህ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ስላልሆነ አንተ ከዚህ ነገር ክፍል ወይም ዕጣ የለህም።


ይህም የሚሆነው ሁለት ሐሳብ ስላለውና በመንገዱም ስለሚያወላውል ነው።


ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ፤ እርሱም ወደ እናንተ ይቀርባል፤ እናንተ ኃጢአተኞች! እጆቻችሁን አጽዱ፤ እናንተ ወላዋዮች! ልባችሁን አጥሩ።


እግዚአብሔር ግን “የኤሊአብን ቁመት መርዘምና መልከ ቀናነቱን አትይ፤ እኔ እርሱን አልፈለግሁትም፤ እኔ የምፈርደው ሰዎች እንደሚፈርዱት አይደለም፤ ሰው የውጪ መልክን ያያል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል” አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos