ኢዮአስም ካህኑን ዮዳሄንና ካህናቱን ጠርቶ፥ “በመቅደሱ ውስጥ የተናዱትን ስፍራዎች ስለ ምን አልጠገናችሁም? ከእንግዲህ ወዲያ ገንዘቡ ለቤቱ መጠገኛ ይሰጥ እንጂ ከሚያመጡት ሰዎች አትቀበሉ” አላቸው።
2 ዜና መዋዕል 23:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሰባተኛውም ዓመት ኢዮአዳ በረታ፤ የመቶ አለቆቹንም፥ የኢዮራምን ልጅ አዛርያስን፥ የኢዮአናንም ልጅ እስማኤልን፥ የዖቤድንም ልጅ አዛርያን፥ የኢዳኢንም ልጅ መዓስያን፥ የዘካርያስንም ልጅ ኤሊሳፋጥን ወደ እግዚአብሔር ቤት ከእርሱ ጋር ወሰደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሰባተኛውም ዓመት ዮዳሄ በረታ፤ የመቶ አለቆች ከሆኑት ከይሮሐም ልጅ ከዓዛርያስ፣ ከይሆሐናን ልጅ ከይስማኤል፣ ከዖቤድ ልጅ ከዓዛርያስ፣ ከዓዳያ ልጅ ከማዕሤያ፣ ከዝክሪ ልጅ ከኤሊሳፋጥ ጋራ ቃል ኪዳን አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰባተኛውም ዓመት ዮዳሄ በረታ፥ የመቶ አለቆቹንም፥ የይሮሐምን ልጅ ዓዛርያስን፥ የይሆሐናንንም ልጅ ይስማኤልን፥ የዖቤድንም ልጅ ዓዛሪያስን፥ የዓዳያንም ልጅ መዕሤያን፥ የዝክሪንም ልጅ ኤሊሳፋጥን ወስዶ ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህኑ ዮዳሄ በሰባተኛው ዓመት የመቶ አለቆች ከነበሩት ከይሮሖም ልጅ ዐዛርያስ፥ ከይሆሐናን ልጅ እስማኤል፥ ከዖቤድ ልጅ ዐዛርያስ፥ ከዐዳያ ልጅ ማዕሴያና ከዚክሪ ልጅ ኤሊሻፋጥ ጋር ስምምነት ለማድረግ ብቃት ያለው መሆኑ ተሰማው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሰባተኛውም ዓመት ዮዳሄ በረታ፤ የመቶ አለቆቹንም፥ የይሮሐምን ልጅ ዓዛርያስን፥ የይሆሐናንንም ልጅ ይስማኤልን፥ የዖቤድንም ልጅ ዓዛሪያስን፥ የዓዳያንም ልጅ መዕሤያን፥ የዝክሪንም ልጅ ኤሊሳፋጥን ወስዶ ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ። |
ኢዮአስም ካህኑን ዮዳሄንና ካህናቱን ጠርቶ፥ “በመቅደሱ ውስጥ የተናዱትን ስፍራዎች ስለ ምን አልጠገናችሁም? ከእንግዲህ ወዲያ ገንዘቡ ለቤቱ መጠገኛ ይሰጥ እንጂ ከሚያመጡት ሰዎች አትቀበሉ” አላቸው።
ስለዚህም ሁሉ የታመነውን ቃል ኪዳን አድርገን እንጽፋለን፤ አለቆቻችንም፥ ሌዋውያኖቻችንም፥ ካህናቶቻችንም ያትሙበታል።”