በሰይፍህም ትኖራለህ፤ ለወንድምህም ትገዛለህ፤ ነገር ግን ቀንበሩን ከአንገትህ ልትጥል ብትወድድ ከእርሱ ጋር ተስማማ።”
2 ዜና መዋዕል 21:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእነዚያም ዘመናት የኤዶምያስ ሰዎች በይሁዳ ላይ ዐመፁ፤ ለራሳቸውም ንጉሥ አነገሡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በይሆራም ዘመነ መንግሥት ኤዶም በይሁዳ ላይ ዐምፆ፣ የራሱን ንጉሥ አነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእርሱም ዘመን ኤዶምያስ በይሁዳ ላይ ዓመፀ፥ ለራሱም ንጉሥ አነገሠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በኢዮራም ዘመነ መንግሥት ኤዶም በይሁዳ ላይ ዐምፆ የራሱን ነጻ መንግሥት አቋቋመ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእርሱም ዘመን ኤዶምያስ በይሁዳ ላይ ዐመጸ፤ ለራሱም ንጉሥ አነገሠ። |
በሰይፍህም ትኖራለህ፤ ለወንድምህም ትገዛለህ፤ ነገር ግን ቀንበሩን ከአንገትህ ልትጥል ብትወድድ ከእርሱ ጋር ተስማማ።”
የእስራኤልም ንጉሥና የይሁዳ ንጉሥ፥ የኤዶምያስም ንጉሥ ሄዱ፤ የሰባትም ቀን መንገድ ዞሩ፤ ለሠራዊቱና ለሚጫኑ እንስሶች ውኃ አጡ።
ኤዶምያስ ግን በይሁዳ ላይ እስከ ዛሬ ድረስ ዐመፀ፤ በዚያም ዘመን ልብና ደግሞ በእርሱ ላይ ዐመፀ፤ የአባቶቹን አምላክ እግዚአብሔርን ትቶ ነበርና።
ኢዮራምም ከአለቆቹና ከሰረገሎቹ ሁሉ ጋር ተሻገረ፤ በሌሊትም ተነሥቶ እርሱንና የሰረገሎቹን አለቆች ከብበው የነበሩትን የኤዶምያስ ሰዎችን መታ፤ ሕዝቡም ወደ ድንኳናቸው ሸሹ።